የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ እና የፌደራል መሬት ባንክ ልማት ኮርፖሬሽን በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

183
የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ እና የፌደራል መሬት ባንክ ልማት ኮርፖሬሽን በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 20/2013ዓ.ም (አብመድ) ስምምነቱ በዋናነት የኮርፖሬሽኑን መሰረተ-ልማት ወደ ዲጂታል ስርዓት እንዲገባ የማድረግ እና የሳይበር ልማት ስትራቴጂክ ፍኖተ ካርታ የማዘጋጀት እንዲሁም የመረጃዎቹን ደኅንነት ማስጠበቅን ያካተተ ነው ተብሏል፡፡
የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ እንዳሉት መሬት ዋነኛ ሀብት በመሆኑ የዚህን ሀብት መረጃ በተገቢው መንገድ መጠቀም እና ማስቀመጥ ለሀገር ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው፡፡
መረጃ አሁን ባለንበት ዘመን ትልቁ እና ቁልፍ መወዳደሪያ ነው፤ ይህንን መረጃ ደኅነነቱን ለማስጠበቅ እና ለመጠቀም የመሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን በሚያከናውናቸው ሥራዎች ላይ ኤጀንሲው በጋራ እንደሚሠራ ገልፀዋል፡፡
የፌደራል መሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሌንሳ መኮንን በበኩላቸዉ የመሬት ነክ መረጃ መያዝ ሀገሪቱ በምታከውነው የመሰረተ ልማት ሥራዎች ላይ ጥራት ያለው ውሳኔ ከመስጠት ባለፈ ደኅንነቱን ለማስጠበቅ ያለውም ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ጋር የተደረገው ስምምነት የመሬት ባንክና ልማት ኮርፖሬሽኑ በቴክኖሎጂ ራሱን ለማዘመን በሚያከውናቸው ሥራዎች ላይ ማዕከል ያደረገ እንደሆነ ከኤጀንሲው ማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበነዳጅ ምርት አቅርቦትና ስርጭት ያሉ እጥረቶችን ለመፍታት እንደሚሠራ የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ገለፀ፡፡
Next articleበአማራ ክልል በአፈር አሲዳማነት በየዓመቱ ከስንዴ ምርት ብቻ እስከ 3 ቢሊዮን ብር የሚገመት ገንዘብ ይታጣል፡፡ ሀገሪቱ ደግሞ 9 ቢሊዮን ብር ከምርቱ ታጣለች።