
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ ለሆኑ የአውሮፓ ሀገራት አምባሳደሮችና ተወካዮች በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ገለፃ አድርገዋል፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 19/2013 ዓ.ም (አብመድ) የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በገለጻቸው እንዳሉት ዘጠና ሁለት የእርዳታ ማሰራጫ ማዕከላት ተቋቁመው በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚያስፈልጋጀው ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ እየተሠራ ይገኛል፡፡
በክልሉ የባንክ አገልግሎት ወደ ሥራ መመለስ ተከትሎ የሰራተኞች ደመወዝ ክፍያን ጨምሮ ከባንክ አገልግሎት ጋር የተገናኙ ችግሮች መፍትሄ ማግኘታቸው፣ የምግብ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች፣ የመድኃኒት አቅርቦት እና ለዜጎች የሚደረገው ሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት እየተከናወነ ስለመሆኑም ገልፀዋል፡፡
መንግሥት ለዜጎች ሰብዓዊ መብት ጥበቃ መጠናከር እንደሚሠራም ለአውሮፓ ሀገራት አምባሳደሮችና ተወካዮች እንዳረጋገጡላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ