
በኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያው ስድስት ወራት ከ344 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 19/2013 ዓ.ም (አብመድ) በኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የስድስት ወራት የእቅድ አፈፃፀም በሐይቅ ከተማ ገምግሟል፡፡
ጽሕፈት ቤቱ በስድስት ወራት ውስጥ 328 ሚሊየን 323 ሽህ 785 ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ ተነግሯል፡፡ ተቋሙ ከእቅዱ 104 ነጥብ 8 በመቶ በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉ ተገልጿል፡፡
በተቋሙ የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም ላይ እንደተጠቀሰው ግብር ከፋዩ በወቅቱ የሚጠበቅበትን ግብር በመክፈል ያሳየው መሻሻል፣ የሙያተኞች ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት ለአፈፃፀሙ መሳካት አስተዋጽኦ እንደነበራቸው ተመልክቷል፡፡
በመድረኩ የሙያተኞችን የአቅም ግንባታ ማሻሻልና በግብር አከፋፈል ዙሪያ የሕግ ተገዥነት ላይ ግንዛቤ ማሳደግ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸው ተመላክተዋል፡፡
በኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ያረጋል ኃይሉ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ፣ የመፈፀም አቅም ግንባታ ክፍተት፣ የግብር አከፋፈል የሕግ ተገዥነት ግንዛቤ ውስንነት እና ከአጋር አካላት ጋር ያለ የቅንጅት ሥራ ክፍተት እንደሚስተዋል በግምገማው ወቅት ተናግረዋል፡፡
የአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል፣ የተነሱ ችግሮችን በመፍታት እና የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ እንደሚሠራ ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡
ጽሕፈት ቤቱ በበጀት ዓመቱ 753 ሚሊየን 724 ሽህ 262 ብር ለመሰብሰብ አቅዷል፡፡
ዘጋቢ፡- ደጀን አምባቸው – ከሐይቅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ