
አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ከአውሮፓ ህብረት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መከሩ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 19/2013 ዓ.ም (አብመድ) በቤልጂየም፣ ሉክሰምበርግና በአውሮፓ ህብረት ተቋማት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ከአውሮፓ ህብረት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
በዚህ ወቅት አምባሳደር ሂሩት በትግራይ ክልል ስለተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻና እየተደረገ ስላለው ተግባራዊ የሰብአዊ ድጋፍ እንቅስቃሴ እንዲሁም የመሰረተ ልማት ግንባታና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል።
መንግስት በአሁን ወቅት ቁልፍ ጉዳዮች ብሎ በለያቸው ተግባሮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቀው፤ “እነዚህም በጣም አስፈላጊ የሆኑ የሰብአዊ ዕርዳታዎችን ማድረስ፣ ወንጀለኞችን በሕግ ፊት ማቅረብ፣ የጭካኔ ድርጊቶችን መመርመር፣ ህብረተሰቡን ማረጋጋት እና የተጎዱ መሠረተ ልማቶችን መልሶ መገንባት ናቸው” ብለዋል፡፡
ወንጀለኞችን ለሕግ የማቅረቡ ስራም ተጠናሮ መቀጠሉን አስረድተዋል፡፡
የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ የልማት ኮሚቴ ሰብሳቢ ቶማስ ቶቤ ኢትዮጵያ በቀጠናው አንጸባራቂ ስኬት በማስመዝገብ ምሳሌ መሆኗን ገልጸው፤ እየተደረገ ያለው ሰብአዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አመልክተዋል።
በፓርላማው ለውጭ ጉዳይ ኮሚቴ፣ የውጭ አገልግሎት ጉዳይ፣ አለማቀፍ የትብብር ኮሚሽን እና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ሃላፊዎችም ላነሷቸው ሃሳቦች አምባሳደር ሂሩት ገለጻ አድርገዋል።
ስለወቅታዊው የኢትዮጵያና የሱዳን የድንበር ጉዳይ እንዲሁም ስለመጪው ምርጫ አምባሳደሯ ማብራሪያ መስጠታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ