ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘዉዴ ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ፌሊክስ ቺሴኬዲ ጋር በሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

87
ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘዉዴ ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ፌሊክስ ቺሴኬዲ ጋር በሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 19/2013 ዓ.ም (አብመድ)ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ከኮንጎ ዲሚክራቲክ ሪፐብሊክ አቻቸው ጋር በነበራቸው ዉይይት በሀገራቱ መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየዉን ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር በሚቻልበት መንገድ ላይ ምክክር አድርገዋል፡፡ በዉይይቱ ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኪንሻሳ መልሶ ለመክፈት መወሰኑን አስታዉቀዋል፡፡
እ.ኤ.አ. በ1962 በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ተከፍቶ የነበረዉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እ.ኤ.አ. በ 1980ዎቹ መጀመሪያ በበጀት እጥረት ምክንያት ተዘግቶ እንደነበረ ይታወሳል፡፡
ሃገራቱ በአቪየሽን ዘርፍ ስምምነት አላቸው፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኪንሻሳ፣ ሉቡምባሺና ጎማ ከተሞች ይበራል፡፡
ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል ስላካሄደዉ የህግ ማስከበር ዘመቻ፣ እየተከናወነ ስለሚገኘው የመልሶ ማቋቋምና የሰብዓዊ እርዳታ ገለጻ አድርገዋል፡፡
የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበርነትን በመጪዉ ሳምንት ከደቡብ አፍሪካዉ ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎሳ እንደሚረከቡ የሚጠበቁት ፕሬዝደንት ቺሴኬዲ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ዉይይት በአደራዳሪነት ሲረከቡ ለጉዳዩ አፍሪካዊ መፍትሄ ለመስጠት የሚደረገውን ጥረት ያስቀጥላሉ ብለው እንደሚጠብቁ ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ገልፀዋል፡፡ መረጃው ከፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤት የተገኘ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበአማራ ክልል ውስብስብ መሬት ነክ ችግሮችን በቀላሉ ለመምራት፣ ሕገወጥነትን ለመከላከልና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየሠራ መሆኑን ኤጄንሲው አስታወቀ፡፡
Next article“የሕዝብ ልጆች ስለሆን በሙያችን ከፊት ተሰልፈናል እንጂ ሊደነቅ የሚገባው ከጎናችን ያልተለየው የሰሜን ወሎም ሆነ የአማራ ሕዝብ ነው” የአማራ ልዩ ኀይል የመቅደላ አምባ ብርጌድ ምክትል አዛዥ