
“ለዲፕሎማሲ ሥራ ዜጎችን በአጋርነት በማሰለፍ የሀገራችንን ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ መሥራት ያስፈልጋል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን
ባሕር ዳር፡ ጥር 18/2013 ዓ.ም (አብመድ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የ2013 ዓ.ም የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ አድርጓል፡፡
በግምገማ መድረኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት የሆኑት የስትራቴጂክ ጥናት ተቋምና የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጄንሲ ሪፖርት ቀርቦ መገምገሙንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን
ወቅቱ የሚጠይቀውን የዲፕሎማሲ ብቃትና ክህሎት የታጠቀና የሀገር ፍቅር ያለው የሰው ኃይልን በዲፕሎማሲው መስክ ማሰማራት ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን ገልፀዋል።
“ለዲፕሎማሲ ሥራ ዜጎችን በአጋርነት በማሰለፍ የሀገራችንን ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ መሥራት ያስፈልጋል” ብለዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ