ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ ለሁለተኛዉ ዙር ትምህርት ቤት ግንባታ የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ፡፡

299
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ ለሁለተኛዉ ዙር ትምህርት ቤት ግንባታ የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 18/2013 ዓ.ም (አብመድ) የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት በመጀመሪያው ዙር በሁሉም ክልሎች ያስገነባቸዉን 20 ሁለተኛ ደረጃ ትምርህርት ቤቶችን በመመረቅ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የመደመር መጽሐፍ ገቢ ትምሕርት ቤቶች በሌሉባቸው አካባቢዎች ትምሕርት ቤቶችን የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት እንዲገነባ ማስረከባቸዉ ይታወሳል።
በመሆኑም ክልሎች መጽሐፉን ሽጠዉ ካስገቡት ገንዘብ ትምህርት ቤቶቹ እንደሚገነቡ ቃል በተገባላቸዉ መሰረት በምዕራብ አርሲ ዞን ሲራሮ ወረዳ ሮጲ ከተማ ለሚገነባዉ ኢፋ ሮጲ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ የሁለተኛዉ ዙር ትምህርት ቤት ግንባታ የመጀመሪያዉ የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል፡፡
የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ ሥርዓቱን ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ እና የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልሽ አብዲሳ ማከናወናቸውን ከቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ እስካሁን ድረስ 45 ፓርቲዎች የምርጫ ምልክታቸውን እንዳስገቡ ተገለፀ፡፡
Next articleየግብርና ምርቶችን ለሚያቀነባብሩ ፋብሪካዎች ሀገር በቀል ግብዓት እንዲያገኙ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡