ኢትዮጵያዊቷ የአሥር ዓመት ታዳጊ አፍሪ ካን ኮድ (AfriCANCode) ውድድር አሸናፊ ሆነች፡፡

233
ኢትዮጵያዊቷ የአሥር ዓመት ታዳጊ አፍሪ ካን ኮድ (AfriCANCode) ውድድር አሸናፊ ሆነች፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 18/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአስር ዓመቷ ኢትዮጵያዊት ሶልያና ግዛው አፍሪ ካን ኮድ (AfriCANCode) በተሰኘው ውድድር የ2020 አሸናፊ ሆናለች፡፡
ሶልያና በዚህ ውድድር አሸናፊ የሆነችበት ማትስቴይንመንት (Mathstainement) የተሰኘ ፕሮጀክት መሆኑን አፍሪካ ኮድ ዊክ (Africa Code Week) ዘግቧል፡፡
ይህ ፕሮጀክት የሞባይል መተግበሪያ ሲሆን መሰረታዊ የሒሳብ እውቀቶች ቀላል፣ መካከለኛና ከባድ በሚል ደረጃ የከፈለና ታዳጊዎች እየተዝናኑ የሒሳብ እውቀት የሚገበዩበት ነው፡፡ መተግበሪያው ስለ ኮሮና ቫይረስ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ መሆኑ ልዩ ያደረገውና ለአሸናፊነት ያበቃት መሆኑ ታውቋል፡፡
በዚህ ኢትዮጵያዊቷ ታዳጊ ሶልያና ባሸነፈችበት ውድድር የመጀመሪያዎቹ 10 ተወዳዳሪዎችና ሀገሮች ይፋ ተደርገዋል፤ ሶልያያናን ተከትለው የደቡብ አፍሪካና የአልጄርያ ታዳጊዎች የሁለተኛና የሦስተኛን ደረጃ መያዛቸው ታውቋል፡፡ መረጃው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበአዲስ አበባ 1 ሽህ 338 ሄክታር መሬት በህገወጥ መንገድ መያዙ ተገለፀ፡፡
Next articleየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ እስካሁን ድረስ 45 ፓርቲዎች የምርጫ ምልክታቸውን እንዳስገቡ ተገለፀ፡፡