
በአዲስ አበባ 1 ሽህ 338 ሄክታር መሬት በህገወጥ መንገድ መያዙ ተገለፀ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 18/2013 ዓ.ም (አብመድ) 21 ሽህ 696 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በህገወጥ መንገድ ተይዘዋል ተብሏል፡፡ ከተማ አስተዳደሩ ባደረገው ጥናት 28 ብሎክ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማለትም ከ782 እስከ 842 የሚሆኑ ቤቶች ሳይገነቡ መቅረታቸው ተመላክቷል፡፡
በከተማው ከሚገኙ 121 ወረዳዎች ውስጥ በ88ቱ ህገወጥ ወረራ ተፈፅሟል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ወረራው ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ እየተፈፀመ የመጣ ነው፡፡
በከተማዋ 322 ቤቶችና ህንጻዎች ባለቤት አልባ ሆነው መገኘታቸውም ተገልጿል፡፡ ባለቤት አልባ ከሆኑት 58ቱ ግንባታቸው የተጠናቀቁ ናቸው፡፡
በከተማዋ 10 ሽህ 565 በህገወጥ መንገድ የተያዙ የቀበሌ ቤቶች መኖራቸውንም ምክትል ከንቲባዋ አመላክተዋል፡፡ 4 ሽህ 76 የቀበሌ ንግድ ቤቶች በህገወጥ መልኩ እንደተያዙም ገልፀዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ራሄል ደምሰው – ከአዲስአበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ