“ኢትዮጵያ በድንበር ጉዳይ ከሱዳን ጋር ለመደራደር በቅድሚያ የሱዳን ኃይል የያዘውን መሬት ሲለቅ ነው” አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

384
“ኢትዮጵያ በድንበር ጉዳይ ከሱዳን ጋር ለመደራደር በቅድሚያ የሱዳን ኃይል የያዘውን መሬት ሲለቅ ነው” አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
ባሕር ዳር፡ ጥር 18/2013 ዓ.ም (አብመድ) ኢትዮጵያ በድንበር ጉዳይ ከሱዳን ጋር ለመደራደር በቅድሚያ የሱዳን የጦር ሃይል ድንበር አልፎ የያዘውን የኢትዮጵያ መሬት ሲለቅ ነው የሚል ፅኑ አቋም ያላት መሆኑን የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም ከብሔራዊ ጥቅም ጋር የተያያዙ (የሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ) ዲፕሎማሲያዊ አብይት ክንውኖች ላይ አተኩረዋል።
ሀገራቱን ለሽምግልና እና ድርድር የሚፈልጉ ወገኖችን “እናመሰግናለን” ያሉት አምባሳደር ዲና ድርድሩ የሚጀመረው የሱዳን ወታደራዊ ሃይል የኢትዮጵያን መሬት ሲለቅ ነው ብለዋል። ኢዜአ እንደዘገበው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየአስር ዓመት የልማት እቅድ በሁሉም ዘርፍ ስኬታማ እንዲሆን የትራንስፖርት ዘርፉን በቀዳሚነት ማዘመን ያስፈልጋል ሲሉ አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡
Next articleየፌደሬሽን ምክር ቤት ለክልሎች ለሚሰጠው የድጎማ በጀትን ግልጽ አሠራር ለመዘርጋት ጥናት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡