የአስር ዓመት የልማት እቅድ በሁሉም ዘርፍ ስኬታማ እንዲሆን የትራንስፖርት ዘርፉን በቀዳሚነት ማዘመን ያስፈልጋል ሲሉ አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡

154
የአስር ዓመት የልማት እቅድ በሁሉም ዘርፍ ስኬታማ እንዲሆን የትራንስፖርት ዘርፉን በቀዳሚነት ማዘመን ያስፈልጋል ሲሉ አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 18/2013 ዓ.ም (አብመድ) ኢትዮጵያ የጀመረችው የአስር ዓመት የልማት እቅድ በሁሉም ዘርፍ ስኬታማ እንዲሆን የትራንስፖርት ዘርፉን በቀዳሚነት ማዘመን እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ።
የትራንስፖርት ዘርፉ የአስር ዓመታት መሪ እቅድ በርካታ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይት እየተደረገበት ይገኛል። በውይይቱ ላይ የተገኙት አቶ ደመቀ መኮንን፣ ሁሉም የሀገሪቱ የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴ በትራንስፖርት ዘርፋ ላይ ጥገኛ በመሆኑ በትኩረት ሊሰራበት ይገባል ብለዋል።
ለዚህ ስኬት መንግስት እቅዱን ከማዘጋጀት ጀምሮ ከፍተኛ በጀት በመመደብ በትኩረት እንደሚሰራ አስረድተዋል።
የትራንስፖርት ሚንስትሯ ዳግማዊት ሞገስ በአስር ዓመቱ የትራንስፖርት መሪ እቅድ ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ የትራንስፖርት ስርዓት ለመዘርጋት በስፋት ይሰራል ብለዋል።
በተለይ ደግሞ እየተባባሰ የመጣውን የትራፊክ አደጋ በግማሽ ለመቀነስ እንደሚሰራም ሚኒስትሯ መናገራቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“ከታኅሣስ ወር ጀምሮ 800 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ዩኒየኖችና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ለማጓጓዝ ችለናል” የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ
Next article“ኢትዮጵያ በድንበር ጉዳይ ከሱዳን ጋር ለመደራደር በቅድሚያ የሱዳን ኃይል የያዘውን መሬት ሲለቅ ነው” አምባሳደር ዲና ሙፍቲ