“በፌዴሬሽን ምክር ቤት የተጀመረው የሪፎርም ሥራ የሕገመንግስት የበላይነትና ሕገ መንግስታዊ ስርዓትን በተሻለ ለማስፈጸም ይረዳል” የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህ

195
“በፌዴሬሽን ምክር ቤት የተጀመረው የሪፎርም ሥራ የሕገመንግስት የበላይነትና ሕገ መንግስታዊ ስርዓትን በተሻለ ለማስፈጸም ይረዳል” የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህ
ባሕር ዳር ፡ ጥር 17/2013 ዓ.ም (አብመድ) በኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የተጀመረው የሪፎርም ሥራ የሀገራዊ ሪፎም አካል ሆኖ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ተልዕኮን የሚያጠናክር ተግባር በመሆኑ ግልጽ ዓላማና ግብ ተቀምጦለት እሱን ለማሳከት በትኩረት እየተሰራ አንዳለ አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህ በላልይበላ ከተማ እየተካሄደ ባለው መድረክ ተናግረዋል።
የሕግ ማዕቀፍ ክፍተቶችን መለየትና መሙላት፣ ግልጽ የአሰራርና የአደረጃጀት ስርዓት መዘርጋት፣ የምክር ቤቱን ተግባር ማቀላጠፍ ፣ ዉጤታማና በብዙኃኑ ዘንድ ቅቡልነት ያለው ለማድረግ እንደ ዓላማ ተይዞ ሪፎርሙ እየተሰራ መሆኑን ደግሞ ረዳት ፕሮፌሰር ዋቅቶሌ ዳዲ በምክክር መድረኩ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት ጠቅሰዋል።
ሪፎርሙ አራት የትኩረት አቅጣጫዎችን ለማሳከት እየተሰራ እንደሆነ አብራርተዋል። በመሆኑም ሀገራዊ አንድነትንና ዘላቂ ሰላም መገንባት፣ ዉጤታማ የፊስካል ሽግግርና ፍታዊ የሀብት ክፍፍል ማረጋገጥ፣ የሕገ መንግስት የበላይነትና ሕገ መንግስታዊነትን ማረጋገጥ፣ ተቋማዊ የማስፈፀም አቅም መገንባት ናቸው ብለዋል።
የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሕግ መንግሥቱ በተሰጠው ስልጣንና ተግባር መሠረት ሀገራዊ ለዉጡን ተከትሎ ዘርፈ ብዙ ለውጦችን እያደረገ እንደሚገኝም ከፌድሬሽን ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል ለማክበር ዝግጅቱ ተጠናቋል” የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ
Next article“ሃይማኖት ያልገደበው ኢትዮጵያዊነት”