“የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል ለማክበር ዝግጅቱ ተጠናቋል” የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ

444
“የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል ለማክበር ዝግጅቱ ተጠናቋል” የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ
ባሕር ዳር፡ ጥር 17/2013 ዓ.ም (አብመድ) የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓል ጥር 23/2013 ይከበራል፡፡
የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር 81ኛ የምስረታ በዓሉን በድምቀት ለማክበር ዝግጅት ማጠናቀቁን የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታውቋል፡፡
በአድዋ ጦርነት ወቅት ለእናት ሀገራቸው ነፃነት የተዋደቁ ፈረሰኞችንና ፈረሶችን ለመዘከር በ1933 ዓ.ም እንደተመሰረተ የሚነገርለት የሰባት ቤት አገው ፈረሰኞች ማኅበር ባህላዊ እሴቱን፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አበርክቶውን እንደጠበቀ ለ81 ዓመታት ዘልቋል፡፡
በየዓመቱ ጥር 23 የሚከበረው የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር በዓል ላለፉት 77 ያክል ዓመታት ያለምንም የመንግሥት ድጋፍ ወረዳዎች በየዓመቱ በየተራ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ሲያከብሩት ቆይተዋል፡፡
ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ግን በመንግሥት እውቅና አግኝቶ ባህላዊ አከባበሩ በዓለም አቀፍ መድረክ እንዲተዋወቅና ለአካባቢው ብሎም ለሀገሪቱ መልካም ገፅታ መገንቢያና የገቢ ምንጭ ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የብሔረሰብ አስተዳደሩ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ዘውዲቱ ወርቁ ተናግረዋል፡፡
ዘንድሮ ለ81ኛ ጊዜ የሚከበረውን ይህ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በፈረስ ትርዒት፣ በፓናል ውይይቶችና በእደ ጥበባት ኤግዚቢሽን ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁንም ኃላፊዋ ተናግረዋል፡፡
ከ33 በማይበልጡ አባላት እንደተመሰረተ የሚነገርለት የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር በአሁኑ ወቅት ከ53 ሺህ በላይ አባላትን በማቀፍ የብሔረሰቡን ባህልና ወግ እያስተዋወቀ ነው፡፡ በዓሉ የተነቃቃ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዲኖር የጎላ ሚና እያበረከተ ነው ተብሏል፡፡
ዘጋቢ፡- ሳሙኤል አማረ-ከእንጅባራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleዩኒቨርሲቲው ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የምግብና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
Next article“በፌዴሬሽን ምክር ቤት የተጀመረው የሪፎርም ሥራ የሕገመንግስት የበላይነትና ሕገ መንግስታዊ ስርዓትን በተሻለ ለማስፈጸም ይረዳል” የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህ