
በላልይበላ ሀገርአቀፍ የአፈጉባዔዎች የጋራ መድረክ ተጀመረ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 17/2013 ዓ.ም (አብመድ) በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ የተከበሩ ታገሠ ጫፎ እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ የተከበሩ አደም ፋራህ መሪነት ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚካሄደው የላልይበላው ሀገርአቀፍ የአፈ-ጉባዔዎች የጋራ የውይይት መድረክ በላልይበላ ማር ሙዚዬም አዳራሽ ተጀመሯል፡፡
በውይይቱ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ምክትል ዋና ፀሐፊ ዶክተር ሄኖክ ስዩም በሚቀርበው የምክር ቤቱ የ5 ዓመታት ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ላይ እንደሚወያይ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m