
የሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ ማሳደግ ለፌዴራል ስርዓቱ ግንባታ ወሳኝ መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አደም ፋራህ ገለጹ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 15/2013 ዓ.ም (አብመድ) የፌዴራል ስርዓት እንዲጎለብት የሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚገባ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አደም ፋራህ ገልጸዋል።
ምክር ቤቱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በፌዴራል ስርዓቱ ላይ በአዳማ ከተማ ውይይት እያደረገ ነው።
የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ለፌዴራል ስርዓቱ መጎልበት ከፍተኛ ሚና እንዳለው ነው በውይይቱ የተገለፀው።
ሕገመንግስቱ ለሁሉም ዜጎች አንድ የፖለቲካ ተሳትፎን የሚያረጋግጥ ቢሆንም ነገር ግን እስካሁን በምክር ቤቶች እና በተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ የሴቶች ተሳትፎ ዝቅተኛ መሆኑን ነው ጥናቶች የሚያረጋግጡት።
የሁሉንም ዜጎች እኩል የፖለቲካ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ስልጣንና ተግባር ያለው የፌዴሬሽን ምክር ቤት በተለይም የሴቶችን የዲሞክራሲ ባህል ማሳደግ ለፌዴራል ስርዓቱ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ነው በውይይቱ የተገለጸው። መረጃው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ