“የኢትዮጵያ ፕሮፌሰሮች ዕውቀታቸውን ለሀገር ልማት በማዋል ንቁ ተሳትፎ ሊያደርጉ ይገባል” ፕሬዚደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ

206
“የኢትዮጵያ ፕሮፌሰሮች ዕውቀታቸውን ለሀገር ልማት በማዋል ንቁ ተሳትፎ ሊያደርጉ ይገባል” ፕሬዚደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ
ባሕር ዳር፡ ጥር 15/2013 ዓ.ም (አብመድ) የኢትዮጵያ ሙሉ ፕሮፌሰሮች ዕውቀታቸውንና እምቅ አቅማቸውን ለሀገር ልማት በማዋል ረገድ ንቁ ተሳትፎ ሊያደርጉ እንደሚገባ የኢፌዴሪ ፕሬዚደንትና የካውንስሉ የበላይ ጠባቂ ሣህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ።
የኢትዮጵያ ሙሉ ፕሮፌሰሮች ካውንስል 2ኛ መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ነው። ፕሬዚደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በጉባኤው ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ ሙሉ ፕሮፌሰሮች ምሁራን በሀገር ልማትና እድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በማድረግ ረገድ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውንም ገልጸዋል።
በቀጣይም የምርምርና የዕውቀት አቅማቸውን በማጠናከር የማህበረሰቡንና የሀገር ልማትን ለማሳደግ ንቁ ተሳትፎ ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ሳሙዔል ኡርካቶ በበኩላቸው በኢትዮጵያ የሙሉ ፕሮፌሰሮችን አቅምና ዕውቀት የመጠቀም ሂደት የሚፈለገውን ያህል እንዳልተከናወነ ጠቅሰው በቀጣይም የምሁራኑን እውቀት በመጠቀም ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ መሰራት አለበት ብለዋል።
በጉባዔው በቀረበው ጥናታዊ ጽሁፎች ላይ ውይይት እየተደረገ መሆኑን የዘገበው ኢብኮነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“ዘመቻው ቢያልቅም ዘመቻው የፈጠራቸው ዕድሎችም፤ ዘመቻው ያስከተላቸው ጫናዎችም አላለቁም” ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት
Next articleየሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ ማሳደግ ለፌዴራል ስርዓቱ ግንባታ ወሳኝ መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አደም ፋራህ ገለጹ፡፡