
ወጣቶች በሀገር ግንባታ ላይ የድረሻቸውን እንዲወጡ የሚመክር መድረክ በእንጂባራ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 14/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ አባላት በተለያዩ ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ በእንጅባራ ከተማ እየመከሩ ነው፡፡
በውይይት መድረኩ ወጣቶች በሀገር ግንባታ ላይ አዎንታዊ ሚናቸውን እንዲወጡ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች የሚዳሰሱበትና ምክክር የሚደረግበት ነው ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ግንባታ የወጣቶች ሚና እና ዓለምአቀፋዊ ልምዶች በሚል መነሻ ሀሳብ ለአንድ ቀን በሚካሄደው በዚሁ መድረክም ከብሔረሰብ አስተዳደሩ የተውጣጡ ከ5 መቶ በላይ ወጣቶች ተሳታፊ ናቸው ተብሏል፡፡
ዘጋቢ፡- ሳሙኤል አማረ- ከእንጂባራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ