የጁንታውን ታጣቂ ሃይል በመምራትና በማዋጋት የተሳተፉት ሜጀር ጄኔራል መሐመድ እሻ እና ብርጋዴል ጄኔራል ሙሉጌታ በርሄ እጃቸውን ሰጡ።

356
የጁንታውን ታጣቂ ሃይል በመምራትና በማዋጋት የተሳተፉት ሜጀር ጄኔራል መሐመድ እሻ እና ብርጋዴል ጄኔራል ሙሉጌታ በርሄ እጃቸውን ሰጡ።
የመከላከያ ሰራዊት አባላት የነበሩትና በጡረታ በክብር የተሰናበቱት ሜጀር ጄኔራል መሐመድ እሻ እና ብርጋዴል ጄኔራል ሙሉጌታ በርሄ እጃቸውን በሰላም መስጠታቸውን የአገር መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ።
የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ እጃቸውን የሰጡት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የጁንታውን ታጣቂ ሃይል በመምራትና በማዋጋት ላይ የነበሩ ናቸው።
መኮንኖቹ በጡረታ ከተገለሉ በኋላ ጁንታውን በመቀላቀል የጦርነት ዝግጅት ሲያደርጉ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።
የአገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ ላይ የህወሃት ጁንታ ጥቃት በፈጸመበት ወቅትም ዋና አስተባባሪ የነበሩ ናቸው።
Previous article5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡
Next articleየጎንደር ከተማንና አካባቢዋን የኢንቨስትመንት መዳረሻ ለማድረግ ያለመ ውይይት ከባለሀብቶች እና ከአጋር አካላት ጋር እየተካሄደ ነው፡፡