
“የኢትዮጵያውያን ባሕል ያልተበረዘ በመሆኑ፣ ቀሪው ዓለም ሊማርበት ይገባል”
ባሕር ዳር ፡ ጥር 11/2013 ዓ.ም (አብመድ)
ማርሲን ኦባሌክ በባሕር ዳር ከተማ የጥምቀት በዓል ተሳታፊ ነው። ማርሲን ኦባሌክ የፖላንድ ዜጋ ናቸው። የጠምቀትን በዓል በባሕር ዳር ሲያከብሩ ለሁለተኛ ጊዜያቸው ነው።
ኢትዮጵያውያን በቡድን ሆነው፣ ሁላቸውም በእድሜ አቻቸው በመሰለፍ ሲዘምሩ፣ ሲያሸበሽቡና ሲጨፍሩ በማየታቸው ግርምትን እንደጫረባቸው ለአብመድ ተናግረዋል። “በተለይ አለባበሳቸው ባሕላዊና ያልተበረዘ መሆኑ ይደንቀኛል” ነው ያሉት።
ማርሲን ኦባሌክ ኢትዮጵያውያን ይህን የመሰለ አኩሪ ባሕላቸው ሳይበረዝ ለቀጣዩ ትውልድ ሊያስተላልፉ ይገባል ብለዋል። “እኔም ወደ ሀገሬ ስመለስ ለሕፃናት የማስተምረው እንዲህ አይነት ጥንታዊነቱን የጠበቀ ባሕል ነው” ብለዋል።
በኢትዮጵያ በጥምቀት በዓል የሚታየውን ሃይማኖታዊና ባሕላዊ ክዋኔዎች ቀሪዉን ዓለም ሊያስተምሩ እንደሚችሉ የጠቆሙት ፖላንዳዊው “የኢትዮጵያውያን ባሕል ያልተበረዘ በመሆኑ፣ ቀሪው ዓለም ሊማርበት ይገባል። አውሮፓና አሜሪካ ብትሄድ ይህን የመሰለ ባሕል አታገኝም፣ ተበርዟል” ብለዋል።
በቀጣይ ትልቁ ሥራቸው ፖላንድንና ኢትዮጵያን በባሕል፣ በምጣኔ ሀብትና በኢንዱስትሪው ዘርፍ ማስተሳሰር እንደሆነ ማርሲን ኦባሌክ አስረድተዋል።
ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ