
መኅበረ ግሸን ለ12 ዓመታት የበጎ ፈቃደኝነት ተግባራትን አከናውነዋል፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 11/2013 ዓ.ም (አብመድ) የመኅበረ ግሸን አባላትን በባሕር ዳር ከተማ ለጥምቀት በዓል ድምቀት የበጎ ፍቃድ ተግባራትን እያከናወኑ አገኘናቸው፡፡ ስለ ማህበራቸውም ጠየቅናቸው፡፡
ሁሉም ነዋሪነታቸው በባሕር ዳር ከተማ ነው፤ የበጎ ፈቃደኝነት ተግባራትን የሚያከናውኑት 27 ሆነው ነው፡፡
ማኅበራቸዉን “መኅበረ ግሸን” ብለው በመሰየም በዓላት ሲመጡ ለ12 ዓመታት ደንብን የማስከበር፣ በዓላት በተሳካ ሁኔታ እንዲከበሩ ጠንክረው እንደሚሠሩ የማኅበሩ ሰብሳቢ ተስፋሁን የማነህ ተናግሯል።
ለጥምቀት በዓል ዝግጅት የሚሆኑ፣ ለጸበል የሚውል ውኃን እንደሚሞሉ፣ የተለያዩ ቀለማትን በመቅባት የጥምቀት ቦታዎችን የማሸብረቅ ተግባርን እንደሚሠሩ የማኅበሩ ሰብሳቢ ገልጿል።
ማኅበሩ በባሕር ዳር ብቻ ሳይሆን በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች በመገኘት የበዓላት ዝግጅት በስኬት እንዲጠናቀቁ በፈቃደኝነት እየሠሩ እንደሚገኙ ተስፋሁን ነግሮናል።
በጎ አድራጊ ወጣቶቹ እያንዳንዳቸው አንዳንድ አረጋዊ በማቀፍ ቋሚ ድጋፍ እንደሚያደርጉ፣ ለፋሲካና ለገና በዓላት ደግሞ በሬ በማረድ እንደሚያስገድፏቸው አስተባባሪው ተናግሯል።
ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ