
ጥምቀት በፍኖተ ሠላም ከተማ
ባሕር ዳር፡ ጥር 11/2013 ዓ.ም (አብመድ) በፍኖተ ሠላም ሥርዓተ ጥምቀቱ ተከናውኖ አሁን ታቦታት በየ መንበራቸው ገብተዋል። ታቦታቱ በቅዳሴ፣ በውዳሴ፣ በዝማሬ፣ በሽብሸባ፣ በእልልታ እና በሆታ ታጅበው ወደ አብያተክርስቲያናቱ ተመልሰዋል፡፡
የፍኖተ ሠላም ከተማ ወጣቶችም ታቦታት የሚጓዙበትን መንገድ ከማፅዳት ጀምሮ በዓሉ በሠላም እንዲከበር ከፀጥታ ኀይሉ ጋር በመተባበር ከፍተኛውን ድርሻ ተወጥተዋል።
ዘጋቢ፡- አማረ ሊቁ- ከፍኖተ ሠላም
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ