“የጥምቀት በዓል ሲከበር ትክክለኛ ክርስትያናዊ ሥነ ምግባርን የተላበሰ ሊሆን ይገባል” የምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አባ ዮሐንስ

310
“የጥምቀት በዓል ሲከበር ትክክለኛ ክርስትያናዊ ሥነ ምግባርን የተላበሰ ሊሆን ይገባል” የምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አባ ዮሐንስ
ባሕር ዳር፡ ጥር 10/2013 ዓ.ም (አብመድ) የጥምቀት በዓል ክርስትያኖች በደስታ አደባባይ ወጥተው በዝማሬና በጭፈራ ያከብሩታል፡፡ ታድያ በዓሉ ሲከበር ክርስትያናዊ ሥነ ምግባርን በመተግበር ሊሆን እንደሚገባ የምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አባ ዮሐንስ በመልዕክታቸው አስተላልፈዋል፡፡
ክርስትና የሚገለፀው ሌሎችን በማክበር፤ በጎ በመስራት፤ የተቸገረን በመደገፍና በመተዛዘን በመሆኑ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን በፀጥታ ችግር ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉና በሀዘን ውስጥ ያሉ ወገኖችን ልናስባቸውና በአቅማችን ልንደግፋቸው ይገባል ነው ያሉት፡፡
የጥምቀት በዓል በደስታ የሚከበር ነው፤ የበዓሉን ደስታ ለማደፍረስ የሚያስቡ ካሉ የበዓሉ ታደሚዎች የአካባቢውን ሰላም በባለቤትነት በመጠበቅ እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡ አጠራጣሪ ሁኔታ ሲያይም ለፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠት በዓሉን ማክበር እንደሚገባ የምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አባ ዮሐንስ አስገንዝበዋል፡፡
በሀገራችን እየገጠመ ያለው የንጹሓን ሞትና መፈናቀል እንዲቆም ሁሉም ዜጋ የድረሻውን መወጣት እንዳለበት የተናገሩት ሊቀ ጳጳስ አባ ዮሐንስ ሰዎች ከሚናገሩት ሀሳብ ጀምሮ ሌሎችን የማያስቀይም፤ ለሌሎች ሰላም አደጋ የማይፈጥር እዲሆን መጠንቀቅ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ህብረተሰቡም ለተሳሳቱ መረጃዎች እንዳይጋለጥ ታማኝ የመረጃ ምንጮችን መጠቀም ባህሉ እንዲያደርግ መክረዋል፡፡
በመጨረሻም የጥምቀት በዓልን ለማክበር ሲባል የተደረገው የፅዳት ዘመቻ በዓሉ ሲከበርም እንዲቀጥል፤ ከበዓሉ በኋላም የአካባቢ ፅዳት ባህል እንዲዳብር ሁሉም ዜጋ ኀላፊነቱን እንዲወጣ ሊቀ ጳጳሱ ጠይቀዋል፡፡
ዘገቢ፡- ሸምስያ በሪሁን
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየወልቃይት፣ የጠገዴ፣ የጠለምት አማራ የባህል ቡድን አባላት ለጥምቀት በዓል ጎንደር ታድመዋል።
Next article‹‹ እነሆ ወደ ዮርዳኖስ ወረደ የእዳ ደብዳቤውም ተቀደደ››