የወልቃይት፣ የጠገዴ፣ የጠለምት አማራ የባህል ቡድን አባላት ለጥምቀት በዓል ጎንደር ታድመዋል።

422
የወልቃይት፣ የጠገዴ፣ የጠለምት አማራ የባህል ቡድን አባላት ለጥምቀት በዓል ጎንደር ታድመዋል።
ባሕር ዳር፡ ጥር 10/2013 ዓ.ም (አብመድ) የጥምቀት በዓል ዘንድሮ በጎንደር ከተማ በልዩ ሁኔታ እየተከበረ ነው። የወልቃይት፣ የጠገዴ፣ የጠለምት አማራ የባህል ቡድን አባላት ጎንደር መገኘት ለጥምቀት በዓል ልዩ ድባብ ፈጥሯል።
በጎንደር ከተማ በዓሉን ለማክበር ከተገኙት የወልቃይት፣ የጠገዴ፣ የጠለምት አማራ የባህል ቡድን አባላት መካከል ትእግስት አዲሱ እንደተናገረችው ለመጀመሪያ ጊዜ በዓሉን ለማክበር ጎንደር ከተማ ተገኝታለች። በዚህም እጅግ ደስተኛ መሆኗን ገልፃለች። በባለፉት ዓመታት የባሕሏ መገለጫ ልብስ እንኳን ለብሳ መንቀሳቀስ በጥብቅ ይከለከል እንደነበር ነው የነገረችን፡፡
በአሁኑ ወቅት ከሕዝቡ ጋር በዓሉን በማክበሯ ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረላት ተናግራለች። የከተማው ነዋሪም ልዩ አቀባበል እንዳደረገላቸው ነው የገለፀችው፡፡
ሌላው የባህል ቡድኑ አባል አላምረው ክንፈ “በዓሉን እንድናከብር የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኀይል እና ሚሊሻ ያደረገው ተጋድሎ ሁሌም የሚታወስ ነው” ብሏል። ጎንደር በመገኘት የጥምቀት በዓልን በማክበሩ የተለየ የደሰታ ስሜት እንደፈጠረበትም ነግሮናል።
የባህል ቡድኑ አስተባባሪ ተስፋሁን ወንዴ ለጥምቀት በዓል ወደ ጎንደር ሲመጡም ሌሎች ወጣቶችን ይዘው እንደመጡም ተናግሯል። ከባህል ቡድኑ አባላት በተጨማሪ የጥምቀት በዓልን ለማክበር በርካታ የወልቃይት፣ የጠገዴ እና የጠለምት ነዋሪዎች ጎንደር ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡- አዳሙ ሽባባው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“ኢየሩሳሌምን መሠላት፣ ገነትን በምድር ሠራት”
Next article“የጥምቀት በዓል ሲከበር ትክክለኛ ክርስትያናዊ ሥነ ምግባርን የተላበሰ ሊሆን ይገባል” የምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አባ ዮሐንስ