“የባለፈው ስህተት አይደገምም” የጎንደር ከተማ አስተዳደር

290
“የባለፈው ስህተት አይደገምም” የጎንደር ከተማ አስተዳደር
ባሕር ዳር ፡ ጥር 10/2013 ዓ.ም (አብመድ) በጎንደር ከተማ አስተዳደር ባለፈው ዓመት ምዕመናን ተሰብሰበው ባህር ጥምቀቱን ለማክበር ለባህር ጥምቀቱ የተሰራው ርብራብ ተደርምሶ በሰው ህይወት ላይ ጉዳት መድርሱ ይታወሳል።
በዚህ ዓመት የባለፈው ዓመት ስህተት እንዳይደገምም በክልሉ መንግሥት ድጋፍ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የወጣበት የብረት ርብራብ መሠራቱን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ አስታወቋ።
በመመሪያው የባህል ዕሴቶች እና ኢንዱስትሪ ልማት ቡድን መሪ ልዕልና ገብረ መስቀል እንደገለጹት የክልሉ መንግሥት ባለፈው ዓመት በምዕመናን ላይ የደረሰውን ጉዳት ታሳቢ በማድርግ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድርግ 2 ሜትር ከፍታ ያለውን የባህር ጥምቀት ማክበሪያ ርብራብ መሠራቱን ተናግረዋል።
የከተማዋ ነዋሪዎችም የተሰራው የባህር ጥምቀቱ ርብራብ ለቡዙ ዓመት የሚያገለግል እና የባዓሉ ታዳሚዎችን ከሥጋት ነፃ የሚያደርግ ነው፤ ለዚህም መንግሥት ምስጋና ይገባዋል ብለዋል።
 
ዘጋቢ ፡- አዳሙ ሽባባው – ከጎንደር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችው መልዕክት አስተላልፈዋል።
Next articleበኩር ጋዜጣ ጥር 10/2013 ዓ/ም ዕትም