
የጥምቀት በዓል በጎንደር ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር በቂ ዝግጅት ማድረጉን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 08/2013 ዓ.ም (አብመድ) በጎንደር የጥምቀት በዓልን ለማክበር ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ የሚመጡ እንግዶችን የከተማዋ ነዋሪዎች መቀበል ጀምረዋል፡፡
በዓሉ ያለምንም የጸጥታ ችግር በድምቀት እንዲከበርም የከተማዋ ነዋሪዎች ከጸጥታ አካላት ጋር ውይይት ማድረጋቸውን የፖሊስ መምሪያው ኀላፊ ኮማንደር አየልኝ ታከለ ተናግረዋል፡፡
የተለያዩ የወጣት አደረጃጀቶችና ሲቪክ ማህበራትም የጥምቀት በዓልን ለማክበር የሚመጡ እንግዶች ተደስተውና የሰላም ችግር ሳይገጥማቸው በዓሉን እዲያሳልፉ ለማድረግ ከፀጥታ አካላት ጋር በጋራ እየሠሩ ነው ብለዋል ኮማንደር አየልኝ፡፡
የከተማ አስተዳድሩ ሰላም እና ሕዝብ ደኀንነት መምሪያ ኃላፊ አቶ ናትናኤል ጎሹ እደገለፁት በበዓሉ ከጸጥታ አካሉ ውጭ በከተማዋ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ አይቻልም፡፡ ለደስታ መግለጫ በሚል ሮኬትም ሆነ እርችት መተኮስም የተከለከለ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ምስጋናው ብርሃኔ-ከጎንደር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ