
የመቅደላ ዓምባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ እያስመረቀ ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 08/2013 ዓ.ም (አብመድ) የመቅደላ ዓምባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ዛሬ ለመጀመሪያ እያስመረቀ ነው፡፡
ዩኒቨርሲቲው ለመጀመሪ ጊዜ 8 መቶ 24 ተማሪዎችን ነው ለምረቃ ብቁ ያደረገው፡፡
በዚህም በዛሬው ዕለት በዋናዉ ግቢ በተፈጥሮ ሳይንስ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 4 መቶ 80 ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው፡፡
በነገው የምረቃ መርሀ ግብር ደግሞ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ግቢው 3 መቶ 44 ተማሪዎች እደሚመረቁ ከዩኒቨርሲቲው የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
በምረቃ መርሀ ግብሩም የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገርና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኀንነት አማካሪ ገዱ አንዳርጋቸውን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኘተዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ሐረገወይን ወንዱ – ከጊንባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ