
የደቡብ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ ሹመት በመስጠት፣ ተጨማሪ በጀትና አዋጅ በማጽደቅ ተጠናቀቀ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 07/2013 ዓ.ም (አብመድ) የደቡብ ክልል ምክር ቤት ለሰባት ቢሮ ኃላፊዎች ሹመት በመስጠት እንዲሁም ከ616 ሚሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀትና አዋጆችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ።
ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 5ኛ ዙር 6ኛ ዓመት 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤ በውክልና ሲሰሩ የቆዩ ሰባት የቢሮ ኃላፊዎች፣ የክልሉ ኦዲት ቢሮ ዋናና ምክትል ኦዲተሮችን እንዲሁም የስድስት ዳኞችን ሹመት አጽድቋል።
በዚህ መሰረት፡-
አቶ ተስፋዬ ይገዙ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ፣
አቶ አንተነህ ፈቃዱ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ፣
አቶ ሀይለማርያም ተስፋዬ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል።
በተጨማሪም፡-
አቶ አክሊሉ አዳኝ የውሀ መስኖና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ፣
አቶ ተሾመ ታከለ የኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ፣
አቶ ገብሬ ናቄ የሳይንስ፣ ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ፣
አቶ ማሄ ቦዳ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ በመሆን የተሾሙ ሲሆን፤
ወይዘሮ ፈዲላ አደም የደቡብ ክልል ኦዲት ቢሮ ዋና ኦዲተር፣
አቶ በላይነህ ሀቹላ ምክትል ዋና ኦዲተር በመሆን ተሹመዋል።
በጎፋ ዞን ለሚገኙ ስድስት የመጀመሪያ ደረጃ የከተማና የወረዳ ፍርድ ቤቶች ዳኞች ተሹመዋል።
አስቸኳይ ጉባኤው የዞንና ክልል ምክር ቤት አባላትን ቁጥር ለመደንገግ የወጣውን አዋጅም ማጽደቁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ምክር ቤቱ በክልሉ ኮሮናን ለመከላከል ለሚሠሩ ሥራዎችና ለሌሎች ተግባራት ማስፈጸሚያ የሚሆን 616 ሚሊዮን 843 ሺህ 300 ብር ተጨማሪ በጀትም በማጽደቅ ጉባኤውን አጠናቋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ