
በአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር የሚመራ የከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ቡድን በደቡብ ወሎ ዞን የተከናወኑ የልማት ተግባራትን እየተመለከቱ ነው።
ባሕር ዳር፡ ጥር 07/2013 ዓ.ም (አብመድ) በቃሉ ወረዳ ገርባ ከተማ የተገነባው 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመርቋል።
ትምህርት ቤቱ 15 መማሪያ ክፍሎች ያሉትና ባለ 2 ወለል ህንጻ ነው። ቤተ ሙከራና ቤተ መጽሐፍትም አሉት፡፡
ትምህርት ቤቱ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገበት ሲሆን ከ7ሚሊዮን ብር በላይ የሸፈነው የአካባቢው ኅብረተሰብ ነው።
ዘጋቢ፡- ስማቸው እሸቴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ