ስዩም መስፍንን ጨምሮ የጁንታው ቀንደኛ አመራሮች ተደመሰሱ

351
ሰበር ዜና
ስዩም መስፍንን ጨምሮ የጁንታው ቀንደኛ አመራሮች ተደመሰሱ
የመከላከያ ሰራዊት ሀይል ስምሪት መምሪያ ሀላፊ ብርጋደል ጀነራል ተስፋዬ አያሌው፣ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ሌሎች የፌዴራል የፀጥታ ተቋማት ዛሬም እንደ ትናንቱ አስደናቂ ጀግንነታቸውን በአንፀባራቂ ድል ታጅበው በድል መወጣት መቀጠላቸውን ለኢዜአ ገልፀዋል።
አሁንም የተቀሩትን የጁንታ አመራሮች የገቡበት ገብተው የማደን ተግባራቸውን አጠናክረው ቀጥለዋልም ብለዋል።
የጁንታው ቡድን ከትጥቅ ትግሉ ጀምሮ በስልጣን ላይ እያለ ኢትዮዽያዊ፣ ከስልጣን ሲወርድና የማይመች ሁኔታ ሲፈጠር ደግሞ አገርን የመበታተንና የማተራመስ ስትራቴጂ ነድፎ የማያሸንፈውንና የማይወጣውን ውጊያ በአባት አርበኝነት ለመፈፀም ሲንቀሳቀስ እንደቆየ ጠቁመዋል።
ከዚህ ተግባሩ ሊቆጠብም ሆነ ከትላንት ሊማር ያልቻለው የጁንታው ቡድን በሰራዊታችን ላይ ውጊያ ከፍቶ በለኮሰው እሳት በመለብለብ ላይ ይገኛል ብለዋል ።
የጁንታው ቡድን አመራሮች ባለፈው ጥቅምት መጨረሻ በመቀሌ በተካሄደው ዘመቻና ድምሰሳ ወቅት በ48 ሰዓት እጅ እንዲሰጡ ቢለመኑም፣ በማናለብኝነትና ትዕቢተኝነት እምቢ በማለት ወደ ጫካ መግባታቸውን ብርጋዴል ጀነራል ተስፋዬ አስታውሰዋል።
በድጋሚም የአገር መከላከያ ሰራዊት የሀገር ሽማግሌ ጭምር በመላክ እጅ እንዲሰጡ፣ ትጥቅ እንዲፈቱና ጉዳያቸው በህግ እንዲታይ ቢያስጠይቅም አሻፈረኝ ብለውና የያዙትን የጥበቃ ሀይል በመተማመን እንዲሁም “ተመልሰን እንነሳለን” በሚል የድሮ ብሂል ተሳስተው ያለ እድሜያቸው በዱር በገደሉ ተሸሽገዋል ብለዋል።
ዋሻዎችን በመጠቀምም ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እይታ ውጪ ለመሆን ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው ሲሉም ገልፀዋል።
ሆኖም ደከመኝ ሰለቸኝ የማይለው ጀግናዊ የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የፌዴራል የፀጥታ ሀይሎች በዛሬው እለት በጋራ ባደረጉት ጠንካራ ፍተሻ በተከዜ ወንዝ ዳርቻ ቀደም ሲል ሰራዊቱን በማስመታት ኢትዮጵያን ለማተራመስ ሲንቀሳቀሱ፣ ሲያቅዱና ሲመሩ የነበሩ ቀንደኛ የጁንታው አመራሮች ከጥበቃ ሀይላቸው ጋር በነበረው ተኩስ ልውውጥ በውጊያ ላይ ከነጥበቃዎቻቸውና የጥበቃ ወታደራዊ አመራሮቻቸው ጋር መደምሰሳቸውን ለኢዜአ ገልፀዋል።
በነበረው ውጊያ ከጥበቃዎቻቸው ጋር አብረው የተደመሰሱ የጁንታው አመራሮች፣
1. አቶ ስዩም መስፍን፣ የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩ እንዲሁም ውጊያውን የመሩና ሰራዊቱ ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ ያዘዙ፣ በመጨረሻም በሰራዊቱ ላይ ውጊያ እንዲከፈት ትዕዛዝ የሰጡ፣
2. አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ፣ የጁንታው ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር የነበሩ
3. አቶ አባይ ፀሃዬ፣ የጁንታው ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር የነበሩ
4. ኮሎኔል ኪሮስ ሀጎስ ከመከላከያ የከዳ ከነጥበቃዎቻቸው ተደምስሰዋል።
በሌላ በኩል በቁጥጥር ስር የዋሉ ወታደራዊና የክልል አመራሮች
1. ኮሎኔል ገብረመስቀል ገብረ ኪዳን፣ ከመከላከያ የከዳ
2. ኮሎኔል ፍስሃ ብርሃኔ፣ ከመከላከያ የከዳ፣
3. ኮሎኔል ዘረአብሩክ ታደሰ፣ ከመከላከያ የከዳ፣
4. ኮማንደር ገብረኪዳን አስገዶም የልዩ ሀይል ክፍለ ጦር አዛዥ የነበረ
5. አቶ መብራህቶም ክንዴ ሀይሉ፣ የክልሉ ውሃ ስራዎች ድርጅት ፋይናንስ ሀላፊ የነበረ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የመከላከያ ሰራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ሀላፊ ብርጋደል ጀነራል ተስፋዬ አያሌው አሁንም በየዋሻው የተደበቁ የጁንታው ቡድን አባላት በሰላማዊ መንገድ እጅ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።
“ትርጉም ለሌለው ጁንታ ጠባቂ በመሆን ውድ ህይወታችሁን አትገብሩ፣ ከቻላችሁ ይዛችኋቸው፣ ካልቻላችሁ በሰላም ለሰራዊቱ እጅ እንድትሰጡ ጥሪ አቀርባለሁ” ብለዋል።
በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ አንዳንድ የትግራይ ተወላጆች ጁንታው ተመልሶ ይመጣል በሚል ያላቸው ግምት የተሳሳተና የጁንታው ቡድን ዘመን ያከተመ መሆኑን አውቀው፣ ከሀገራቸውና ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጎን በመሆን ትግራይን እንዲያደራጁ፣ እንዲያለሙና መላው ህዝብም የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
Previous articleየአማራ ልማት ማኀበር (አልማ) በየዓመቱ የአየር ሰዓት በነፃ በመስጠት ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ከአማራ ብዙኀን መገናኛ ድርጅት እንደሚያገኝ አስታወቀ፡፡
Next articleየኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ – ኢሰመጉ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፣ መተከል ዞን፣ በቡለን፣ ድባጤ፣ እና ዳንጉር ወረዳዎች ላይ በንጹኃን ሰዎች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት አሁንም ተባብሶ መቀጠሉ እጅግ እንዳሳሰበው አስታወቀ፡፡ የኢሰመጉ ሙሉ መግለጫ ቀጥሎ ይቀርባል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ – ኢሰመጉ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፣ መተከል ዞን፣ በቡለን፣ ድባጤ፣ እና ዳንጉር ወረዳዎች ላይ በንጹኃን ሰዎች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት አሁንም ተባብሶ መቀጠሉ እጅግ አሳስቦታል፡፡ ኢሰመጉ ታህሳስ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣው አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ በመተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ፣ በኩጂ ቀበሌ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ከ100 በላይ ንጹኃን ሰዎች መገደላቸውን፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸውን እና ለከፍተኛ ችግር የተጋለጡ መሆናቸውን አውግዞ፤ መንግሥት በአካባቢው በተደጋጋሚ ጊዜ የሚከሰተውን የንጹኃን ሰዎች ሰቆቃ ለማስቆም የሚያስችል ፈጣን፣ ተጨባጭ እና ዘላቂ መፍትሔ እንዲያበጅ ማሳሰቡ አይዘነጋም። ሆኖም፤ ከሰሞኑ ይኸው ችግር ዳግም ተከስቶ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ተጎጂዎች እና የተጎጂ ቤተሰቦች ለኢሰመጉ ተናግራዋል፡፡ ታህሳስ 25 ቀን 2013 ዓ.ም ከቻግኒ ወደ ግልገል በለስ የሚሄድ መኪና ውስጥ የነበሩ ተጓዦች ማንዱራ ከተማ ላይ በታጣቂዎች እንዲወርዱ ተደርጎ አንድ ሰው መገደሉን እና ሁለት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከጥር 2 – 3 ቀን 2013 ዓ.ም በቡለን እና ጉባ ወረዳዎች፣ ኦሜድላ እና አይነሸምስ በተባሉ ቀበሌዎች ላይ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ከ50 በላይ ሰዎች መገደላቸውን እና መኖሪያ ቤቶችም መቃጠላቸውን ኢሰመጉ መረጃዎች ደርሰውታል፡፡ በሌላ በኩል ‹‹በድባጤ ወረዳ፣ ቆርቃ ቀበሌ፣ ዳሌቲ በተባለች መንደር ትላንት ጥር 4 ቀን 2013 ዓ.ም ከሌሊቱ 11፡30 ጀምሮ የኦነግ ሸኔ እና የቤኒን ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ሰዎች መገደላቸውን፣ እስከአሁን ድረስ እኔ ራሴ ባለሁበት የ82 ሰዎች አስከሬን በፍለጋ መገኘቱን እና የቀብር ቦታዎች እየተዘጋጁ መሆኑን አይቻለሁ›› ሲሉ አንድ የዓይን እማኝ ለኢሰመጉ ተናግረዋል፡፡ ኢሰመጉ፤ በትላንትናው ጥቃት ሰለባ የሆኑ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሊበለጥ እንደሚችል፣ በአብዛኛው ሴቶችና ህጻናት መሆናቸውን እና ከ24 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ቆስለው በጋሊሳ ጤና ጣቢያ እና ቡለን ሆስፒታል ውስጥ ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ከአካባቢው ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለማወቅ ችሏል፡፡