የአማራ ልማት ማኀበር (አልማ) በየዓመቱ የአየር ሰዓት በነፃ በመስጠት ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ከአማራ ብዙኀን መገናኛ ድርጅት እንደሚያገኝ አስታወቀ፡፡

257
የአማራ ልማት ማኀበር (አልማ) በየዓመቱ የአየር ሰዓት በነፃ በመስጠት ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ከአማራ ብዙኀን መገናኛ ድርጅት እንደሚያገኝ አስታወቀ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 05/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ልማት ማኀበር (አልማ) በየዓመቱ ከግማሽ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ከአማራ ብዙኀን መገናኛ ድርጅት እንደሚያገኝ አስታውቋል፡፡ ማኀበሩ ባለፉት ዓመታት ያከናወናቸውን እና በቀጣይ ለመሥራት ያቀዳቸውን ሥራዎች አስመልክቶ ከድርጅቱ ሠራተኞች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
የአማራ ልማት ማኀበር (አልማ) በክልሉ በትምህርት፣ በጤና እና በሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ እንደሚገኝ የማኀበሩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ፋንታ ገልጸዋል፡፡
በተለይ በክልሉ የሚታየውን የትምህርት ቤቶች የጥራት ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ የኀብረተሰብ ክፍሎችን እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ድጋፍ በመጠየቅ ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶችን በተለያዩ አካባቢዎች ገንብቶ ሥራ ላይ እንዲውሉ እያደረገ ነው፡፡
ማኀበሩ በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአልማን የሥራ እንቅስቃሴ በማስረዳቱ በተገኘ ድጋፍ የዳስ ትምህርት ቤቶችና የፈራረሱ መማሪያ ክፍሎች ደረጃቸውን ወደጠበቁ መማሪ ክፍሎች ተቀይረዋል ብለዋል አቶ መላኩ፡፡
የማኀበሩን የገቢ ምንጭ ከፍ ለማድረግ በአማራ ክልል ገቢ የሚያስገኙ የመንግሥት ፕሮጀክቶችን እየተረከበ ነው ያሉት አቶ መላኩ በዚህም በደቡብ ጎንደር ዞን የሚገኘውን ዋንዛየ የተፈጥሮ የፍል ውኃ እና የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ በማሳደግ ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት እየሠራ ነው፡፡
አልማ የሚሠራቸውን ልማቶች በማስተዋወቅ የአጋር አካላትን ቁጥር በመጨመር ጠንካራ ተቋም እንዲሆን በአማራ ብዙኀን መገናኛ ድርጅት የመገናኛ ዘርፎች እያስተዋወቀ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የአማራ ብዙኀን መገናኛ ድርጅት ለአልማ እያደረገ ላለው ድጋፍም ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ መላኩ ፋንታ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሠራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸዉ ጽሕፈት ቤት የተገነባዉ ሳህላ ብርሀን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ፡፡
Next articleስዩም መስፍንን ጨምሮ የጁንታው ቀንደኛ አመራሮች ተደመሰሱ