በቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸዉ ጽሕፈት ቤት የተገነባዉ ሳህላ ብርሀን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ፡፡

261
በቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸዉ ጽሕፈት ቤት የተገነባዉ ሳህላ ብርሀን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 05/2013 ዓ.ም (አብመድ) በቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤት ግንባታቸው ከተጠናቀቁ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ የሆነዉን በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሳህላ ሰየምት ወረዳ ያስገነባዉን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዛሬዉ ዕለት አስመርቋል፡፡
ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው፣የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገርና የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወርቀሰሙ ማሞን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው የተመረቀው።
ትምህርት ቤቱ በውስጡ የአስተዳደር ህንጻ፣የመማሪያ ክፍሎች ፣ላብራቶሪ ፣ቤተ መጽሃፍት፣ የስብሰባ አዳራሽ እና የመጸዳጃ ህንጻዎችን ያካተተ ነው ተብሏል።
ግንባታዉ 13 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል፡፡
ጽሕፈት ቤቱ በዛሬዉ ዕለት ያስመረቀዉ ሳህላ ብርሃን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታቸዉ ተጠናቆ ከተመረቁት ሰባተኛው ሲሆን ቀሪዎቹ በቅርብ ቀን በሁሉም ክልሎች ያስመርቃል ተብሏል፡፡
ትምህርት ቤቱ በሙሉ አቅሙ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር በአንድ ፈረቃ 1 ሺህ ተማሪዎችን የመቀበል አቅም አለዉ፡፡
ዘጋቢ፡- ስማቸው እሸቴ – ከሳህላ ሰየምት
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየመሀመድ ሁሴን አሊ አልአሙዲን ስታዲየም አለም አቀፍ ውድድሮችን እንዲያስተናግድ ለማስቻል በወልዲያ ከተማ ደረጃቸውን የጠበቁ ባለኮኮብ ሆቴሎች እንደሚያስፈልጉ ተገልጿል፡፡
Next articleየአማራ ልማት ማኀበር (አልማ) በየዓመቱ የአየር ሰዓት በነፃ በመስጠት ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ከአማራ ብዙኀን መገናኛ ድርጅት እንደሚያገኝ አስታወቀ፡፡