በቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤት የተገነባው የብርሐን ደባርቅ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።

341
በቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤት የተገነባው የብርሐን ደባርቅ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።
ባሕር ዳር፡ ጥር 05/2013 ዓ.ም (አብመድ) ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው እና የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ የክልልና የፌዴራል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው ትምህርት ቤቱ የተመረቀው።
የቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤት የትምህርት ተደራሽነትንና ጥራትን ለማሳደግ በሚያደረገዉ ጥረት በጽሕፈት ቤቱ ግንባታቸው ከተጠናቅቁ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ የሆነዉን በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ አስተዳደር ያስገነባዉን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዛሬዉ እለት አስመርቋል፡፡
ትምህርት ቤቱ በዉስጡ የአስተዳደር ህንጻ፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ ላብራቶሪ፣ የቤተ መጽሀፍ ፣ የስብሰባ አዳራሽ እና የመጸዳጃ ህንጻዎችን ያካተተ ሲሆን ግንባታዉ 13 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል ተብሏል፡፡
ጽሕፈት ቤቱ በዛሬዉ እለት ያስመረቀዉ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታቸዉ ተጠናቆ ከተመረቁት ስድስተኛው ሲሆን ቀሪዎቹ በቅርብ ቀን በሁሉም ክልሎች እንደሚያስመርቅም ታውቋል፡፡
ትምህርት ቤቱ በሙሉ አቅሙ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር በአንድ ፈረቃ 1 ሺህ ተማሪዎችን የመቀበል አቅም አለዉ፡፡
ዘጋቢ፡- ስማቸው እሸቴ ከደባርቅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleከትህነግ ጎን ተሰልፈው የነበሩ 120 የአፋር ነፃ አውጪ ታጣቂዎች የታቀደላቸውን ጥፋት ተግባራዊ ሳያደርጉ በሰላም ወደ ክልሉ መግባታቸው ተገለፀ።
Next articleበባሕር ዳር ከተማ በመብራት የአገልግሎት ክፍያ መጉላላታቸውን ደንበኞች ተናገሩ፡፡