ከትህነግ ጎን ተሰልፈው የነበሩ 120 የአፋር ነፃ አውጪ ታጣቂዎች የታቀደላቸውን ጥፋት ተግባራዊ ሳያደርጉ በሰላም ወደ ክልሉ መግባታቸው ተገለፀ።

327
ከትህነግ ጎን ተሰልፈው የነበሩ 120 የአፋር ነፃ አውጪ ታጣቂዎች የታቀደላቸውን ጥፋት ተግባራዊ ሳያደርጉ በሰላም ወደ ክልሉ መግባታቸው ተገለፀ።
ባሕር ዳር፡ ጥር 05/2013 ዓ.ም (አብመድ)
ከትህነግ ጎን ተሰልፈው የነበሩ 120 የአፋር ነፃ አውጪ ታጣቂዎች ሀገርን እንዲያፈርሱ በጥፋት ሀይሉ የታቀደላቸውን ጥፋት ተግባራዊ ሳያደርጉ ወደ አፋር ክልል በሰላም እንዲገቡ መደረጉን የሀገር መከላከያ ሠራዊት አስታውቋል።
ለውጡን ተከትሎ ከኤርትራ በርሀ ወደ ሀገር የገቡት “የኡጉጉሙ” ታጣቂዎች ለአንድ ዓመት ያህል በትህነግ ስልጠና ተሰጥቷቸው ለጥፋት ቢዘጋጁም በመከላከያ እና በአፋር ክልል መንግስት የጋራ ጥረት እንዲመለሱ ተደርገው የሰላም ውይይት መጀመራቸው ነው የተገለፀው።
ታጣቂዎቹ ሲገቡ የተቀበላቸው፣ ያኔ ለመሰደዳቸው ምክንያት የነበረው ትህነግ እድሉን በመጠቀም ለሌላ ጥፋት እንዳሰማራቸው ከሀገር መከላያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
የኡጉጉሙ 120 ታጣቂዎች ለአንድ ዓመት ያህል በትህነግ ስልጠና ተሰጥቷቸው ለጥፋት ቢዘጋጁም፤ በመከላከያ እና በአፋር ክልል መንግስት የጋራ ጥረት በሰላማዊ መንገድ ከእነ ትጥቃቸው ከትግራይ ክልል ወደ አፋር ክልል እንዲገቡ መደረጉ ነው የተገለፀው።
ትህነግ በሀገር ላይ ጥቃት ሲፈፅም የኡጉጉሙ ታጣቂዎች “የአፋር ህዝብ ኢትዮጵያን የመክዳት ታሪክ እንዳላወረሳቸው” በመግለፅ የሰለም ጥሪውን እንደተቀበሉ የታጣቂዎቹ አስተባሪዎች ተናግረዋል።
የመከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ የሰብዓዊ መረጃ ሀላፊ ብረጋዲር ጄነራል ደምስ አመኑ ትህነግ የኡጉጉሙ ታጣቂዎችን በመጠቀም ዋናውን የጁቡቲ መንገድ የመቆጣጠር እቅድ ነበረው ብለዋል።
የመከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ የሰብዓዊ መረጃ ስምሪት አባል ኮሎሌል ጤናው ዳምጠው እንደሚሉት ደግሞ ታጣቂዎቹ ስልጠና ሲሰጣቸው የአፋር ክልል ሰላማዊ እንቅስቃሴን ችግር ውስጥ እንዲያስገቡ ጭምር ታስቦ ነበር።
ከሁለት ዓመት ወዲህ መቐለ የጥፋተኞች ምሽግ ሆና እንደቆየች የሚጠቅሱት የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ትህነግ ታጣቂዎችን በመጠቀም አፋርን የማበጣበጥ እቅድ እንደነበረው ተናግረዋል።
መከላከያ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የአፋር መንግስት ታጣቂዎች ወደ ጥፋት እንዳይገቡ ለማድረግ የሰሩት ስራ ውጤት ማስመዝገቡን ያነሱት ርዕሠ መስተዳደሩ ትህነግ ፍላጎቱ አልተሳካለትም ብለዋል።
ኢብኮ እንደዘገበው የኡጉጉሙ ታጣቂዎች በቀጣይ ትጥቃቸውን ፈትተው በፈለጉት ዘርፍ ገብተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ድጋፍ እንደሚደረግላቸውም ተገልጿል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበአለም ጤና ድርጅት ምዘና በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ከሚያደርጉ ሰዎች ውስጥ ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሰዎች ከ10 በመቶ በላይ መሆኑ ሀገሪቱ የጤና አደጋ እንዲገጥማት ማድረጉ ተገለፀ።
Next articleበቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤት የተገነባው የብርሐን ደባርቅ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።