“በየአመቱ በአማካይ ከ14 ሺህ በላይ እናቶች በወሊድና ከወሊድ ጋር በተገናኘ ህይወታቸውን ያጣሉ” ዶክተር ሊያ ታደሰ

230
“በየአመቱ በአማካይ ከ14 ሺህ በላይ እናቶች በወሊድና ከወሊድ ጋር በተገናኘ ህይወታቸውን ያጣሉ” ዶክተር ሊያ ታደሰ
ባሕር ዳር፡ ጥር 04/2013 ዓ.ም (አብመድ)
በኢትዮጵያ በየዓመቱ በአማካይ ከ14 ሺህ በላይ እናቶች በወሊድና ከወሊድ ጋር በተገናኘ ችግር ህይወታቸውን እንደሚያጡ የጤና ሚንስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት የጤናማ እናትነት አምባሳደር ሆና ተመርጣለች።
የጤናማ እናትነት ወር ዘመቻ ዘንድሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ35ኛ ጊዜ በኢትዮያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ ይከበራል።
የዘንድሮው ጤናማ እናትነት ወር ዘመቻ “በደም መፍሰስ ምክንያት እናት ለምን ትሙት?” በሚል መሪ መልዕክት ተጀምሯል።
በአለም ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው እናቶች ከእርግዝና እና ከወሊድ ጋር በተያያዙ ችግሮች ምክንያት ህይወታቸውን ያጣሉ።
ከእዚህ ውስጥም በዋናነት 50 በመቶ የሚሆኑት እናቶች የሚሞቱት በደም መፍሰስ ሳቢያ መሆኑ ይገለጻል።
ወደ ጤና ተቋማት ሄደው የማይወልዱ እናቶች መኖር፣ የመሰረተ ልማት እና የህክምና ግብዓቶች እጥረት እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች የስነ-ምግባር ችግር መኖርም በምክንያትነት ከሚጠቀሱት መካከል ናቸው።
በኢትዮጵያ በርካታ ቁጥር ያላቸው እናቶች ከወሊድ እና ከወሊድ ጋር በተያያዙ ምክንያቶች ህይወታቸውን እንደሚያጡ በዘመቻ ማስጀመሪያው መርሀ-ግብር ላይ ሚኒስትሯ መናገራቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበማይካድራው የዜጎች ጭፍጨፋ ወንጀል የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦችና ተባባሪዎቻቸው ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡
Next article“ተገቢዉን ድጋፍና እንክብካቤ ቢደረግለት ጣና ከሁለት ዓመታት በኋላ አይለምንም” የጣና ሐይቅና ሌሎች የውኃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ