የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ዘመናዊ አሠራርን በመተግበሩ ግብር ከፋዮች ግብራቸውን በወቅቱ እንዲከፍሉ አስችሏቸዋል፡፡

373
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ዘመናዊ አሠራርን በመተግበሩ ግብር ከፋዮች ግብራቸውን በወቅቱ እንዲከፍሉ አስችሏቸዋል፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 04/2013 ዓ.ም (አብመድ) የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ የደንበኞችን ሙሉ መረጃ ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂ በመቀየር የመረጃ አያያዙን ማዘመን ችሏል፡፡ የመምሪያው ኀላፊ አቶ ኃይለሚካኤል አለባቸው እንደገለጹት የተቋማቸው የመረጃ አያያዝ ደካማ መሆን የመልካም አስተዳደር ችግር ሲፈጥር ቆይቷል፡፡
ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂ መቀየሩ መንግሥት ትክክለኛውን ገቢ እዲያገኝ አስችሏል፤ ግብር ከፋዮችም ግብር ለመክፈል ሲመጡ ይደርስባቸው የነበረውን መጉላላት አስቀርቶ በአጭር ጊዜ ከፍለው እዲሄዱ አድርጓል ነው ያሉት፡፡
ነጋዴዎቹም በነበረው የአሠራር ችግር መረጃቸውን ለማግኘት ይንገላቱ እንደነበር እና ይህም የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ መቆየቱን አውስተዋል፡፡
ግብር ከፋይ ነጋዴዎቹ እንደሚሉት መረጃቸው ጠፍቷል እየተባሉ ይንገላቱ ነበር፤ በአሁኑ ወቅት ግን ግብር አስከፋይ ተቋሙ አሠራሩን ወደ ዘመናዊ መንገድ መቀየሩ ቀደም ሲል ይደርስባቸው የነበረውን መጉላላት አስቀርቶላቸዋል፡፡ ግብራቸውንም በወቅቱ ለመክፈል እደገዛቸው ነው የተናገሩት፡፡
ዘጋቢ፡- ምስጋናው ብርሀኔ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“በጥምቀት በዓል የትራንስፖርት አገልግሎት ችግር እንዳይገጥም በመናኸሪያዎች ላይ ክትትል እና ቁጥጥር እያደረኩ ነው” የአማራ ክልል መንገድ እና ትራንስፖርት ቢሮ
Next articleበማይካድራው የዜጎች ጭፍጨፋ ወንጀል የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦችና ተባባሪዎቻቸው ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡