“በጥምቀት በዓል የትራንስፖርት አገልግሎት ችግር እንዳይገጥም በመናኸሪያዎች ላይ ክትትል እና ቁጥጥር እያደረኩ ነው” የአማራ ክልል መንገድ እና ትራንስፖርት ቢሮ

480
“በጥምቀት በዓል የትራንስፖርት አገልግሎት ችግር እንዳይገጥም በመናኸሪያዎች ላይ ክትትል እና ቁጥጥር እያደረኩ ነው” የአማራ ክልል መንገድ እና ትራንስፖርት ቢሮ
ባሕር ዳር፡ ጥር 04/2013 ዓ.ም (አብመድ) በበዓላት ወቅት ሊያጋጥም የሚችለውን የትራንስፖረት ችግር ለመቅረፍ በዞኖች የሚገኙ ተሽከርካሪዎች በመርሃ ግብራቸው መሰረት እንዲሠሩ ክትትል እና ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን የአማራ ክልል መንግድና ትራንስፖርት ቢሮ የህዝብ የትራንስፖረት አገልግሎት አቅርቦት ስምሪት ባለሙያ ጌታቸው መርሻ ተናግረዋል፡፡
አቶ ጌታቸው እንደገለጹት በገና በዓል ከመርሃ ግብሩ ውጭ ታሪፍ በመጨመር፣ ከተፈቀደው በላይ በመጫን እና ከመርሃ ግር ውጭ በሌላ መስመር በሠሩ አሽከርካሪወች ላይ ቅጣት ተጥሏል፡፡
ወቅቱ የጥምቀት በዓል የደረሰበትና ከቦታ ቦታ እንቅስቃሴወች በመጨመራቸው ከመናህሪያ ውጭ ከተፈቀደላቸው በላይ የመጫን እና ከታሪፍ በላይ የማስከፈል ችግሮች አሁንም እተስተዋሉ ነው ብለዋል፡፡
ችግሩን ለማስቆም ቢሮው ከትራፊክ ፖሊስና የመንገድ ደኀንነት ተቆጣጣሪዎች ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን ነግራናል፡፡
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የመንገድ ትራፊክ ደኀንነት መምሪያ በበኩሉ ህግን ተላልፎ በሚገኝ ማንኛውም አሽከርካሪ ህጋዊ ርምጃ እንደሚወሰድ ገልጿል፡፡
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የመንገድ ትራፊክ ደህንነት መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር ሙሉጌታ በዜ እንደነገሩን በገና በዓል በሌሊት ህገወጥ ጉዞ ባደረጉ፣ ከታሪፍ በላይ ባስከፈሉ እና ከአቅም በላይ በጫኑ ከ1 ሺህ 600 በላይ አሽከርካሪዎች ከ600 እስከ 5000 ብር ተቀጥተዋል፡፡
ሁለት አሽከርካሪዎች ደግሞ ለ6 ወር እንዳያሽከረክሩ ታግደዋል ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የትራንስፖርት ዝውውር የሚካሄድበት በመሆኑ ህገወጥ አሽከርካሪወች የትራፊክ ህጉን እዳይጥሱ ከመንገድ እና ትራንስፖርት ባለሙያዎች ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን ኮማንደር ሙሉጌታ ገልጸዋል፡፡
ህግን ተላልፎ የሚገኝ ማንኛውም አሽከርካሪ እና ባለሃብት ከ15 ቀናት በላይ ከስምሪት እንደሚያሳግድ እና ከ12 ሺህ ብር በላይ በህግ እንደሚያስቀጣም አስገንዝበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሰራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች ከአንድ ቢሊዮን 300 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ፡፡
Next articleየጎንደር ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ዘመናዊ አሠራርን በመተግበሩ ግብር ከፋዮች ግብራቸውን በወቅቱ እንዲከፍሉ አስችሏቸዋል፡፡