
ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር በማእከላዊ ጎንደር ዞን በላይ አርማጭሆ ወረዳ እየተከናወኑ ያሉ የችግኝ ዝግጅትና የተፋሰስ ልማትን እየጎበኙ ነው።
ባሕር ዳር፡ ጥር 04/2013 ዓ.ም (አብመድ) ርእሰ መሥተዳድሩ በወረዳው በሹማራ ሎምየ ቀበሌ የባንብላ ተፋሰስ ልማትን ተመልክተዋል።
ባለፉት ዓመታት በተከናወነው የተፋሰስስ ልማት ሥራ ቡና፣ ማንጎ፣ ሙዝ፣ጌሾና ሌሎች ገበያ ተኮር አትክልትና ፍራፍሬ በአካባቢው አርሶ አደሮች እየለማ ይገኛል።
አርሶ አደር ተስፋ ኃይሌና ብርሃን ፈንቅለው እንዳሉት እነርሱን ጨምሮ በርካታ አርሶ አደሮች ተግባራዊ ባደረጉት የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ተጠቃሚነታቸው እያደገ ነው።
ርእሰ መሥተዳድሩ የ2013 ዓ.ም የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ሥራንም በማእከላዊ ጎንደር ዞን በላይ አርማጭሆ ወረዳ በይፋ ያስጀምራሉ።
በተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ሥራ ማስጀመሪያው የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወርቀሰሙ ማሞና የኢፌዴሪ ግብርና ሚኒስትር ዲኤታ ሳሚ ረዲን ጨምሮ የፌዴራል፣ የክልል እና የዞን ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡- ስማቸው እሸቴ – ከላይ አርማጭሆ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ