
ከ290 ሽህ ዶላር በላይ የህክምና ቁሳቁስ ተበረከተ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 03/2013 ዓ.ም (አብመድ) በአሜሪካ የሚገኝ ምህረት የህክምና ቁሳቁስ አቅራቢ የተባለ ድርጅት 290 ሽህ 281 ዶላር የሚያወጡ የመድኃኒት እና የግል ጤና መጠበቂያ መሳሪያዎችን እንዳበረከተ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡
የህክምና ቁሳቁሶቹ በኢትዮጵያ ለታካሚዎችና ለጤና ባለሙያዎች አገልግሎት ላይ እንደሚውሉ አምባሳደሩ ገልፀዋል፡፡
አምባሳደሩ ለተበረከተው የህክምና ቁሳቁስ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ