ከ5 ሚሊዮን በላይ ወጣቶችን ተሣታፊ ያደርጋል የተባለ የምክንያታዊ ወጣቶች መድረክ ተጀመረ።

118
ከ5 ሚሊዮን በላይ ወጣቶችን ተሣታፊ ያደርጋል የተባለ የምክንያታዊ ወጣቶች መድረክ ተጀመረ።
ባሕር ዳር፡ ጥር 03/2013 ዓ.ም (አብመድ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በጋራ የሚያስተባብሩት ይህ መድረክ በቀጣይ በሁሉም ከተማ አስተዳደሮች ይካሄዳል ተብሏል።
በዚህም በመጀመሪያው ዙር ብቻ ከ5 ሚሊዮን በላይ ወጣቶችን ተሣታፊ እንደሚያደርግ ነው የተገለፀው፡፡
በሀገር ግንባታ ሂደት የወጣቱ ሚና ምን መሆን አለበት? የሀገር ግንባታ ሂደት ምን መልክ መያዝ ይኖርበታል? በሚሉና በሌሎች ጉዳዮች ላይ በሚካሄደው መድረክ ልዩ ልዩ ጽሑፎችን የሚያቀርቡ የዩኒቨርሲቲ ወጣት ምሁራን በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ ውይይት እያደረጉ ነው።
ዘጋቢ፡- እንዳልካቸው አባቡ – ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበኩር ጋዜጣ ጥር 03/2013 ዓ/ም ዕትም
Next articleየህጻናትን ፍልሰት ለመከላከል ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል፡፡