
በጃንሜዳ ከ5 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ነዳያን የማዕድ ማጋራት መርሐ-ግብር ተካሄደ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 02/2013 ዓ.ም (አብመድ) በጃንሜዳ ከ5 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የጎዳና ተዳዳሪዎችና ነዳያን የማዕድ ማጋራት መርሐ-ግብር ተካሂዷል፡፡ በመርሐ-ግብሩ ላይ ለበጎ ሥራው ድጋፍ ያደረጉ የቤተክርስቲያን አባቶች፣ መምህራን እና ታዋቂ አርቲስቶች መገኘታቸው ታውቋል፡፡
የማዕድ ማጋራት መርሐ-ግብሩ የጎዳና ተዳዳሪዎች እና ነዳያንን የገናን ጾም ለማስፈታት ታልሞ የተዘጋጀ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
የማዕድ ማጋራት መርሐ-ግብሩን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊያን ወጣቶች እና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት እንዲሁም የቡና እና የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለቦች አባላት እና ደጋፊዎች ማዘጋጀታቸውን የዘገበው ኢቢሲ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ