
በ20ኛው ታላቁ ሩጫ ጽጌ ገ/ሰላማ በሴቶች አቤ ጋሻሁን በወንዶች አሸነፉ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 02/2013 ዓ.ም (አብመድ) ዛሬ በተካሄደው 20ኛው ታላቁ ሩጫ ጽጌ ገ/ሰላማ በሴቶች አቤ ጋሻሁን በወንዶች አሸነፉ።
ለ20ኛ ጊዜ በተካሄደው ታላቁ ሩጫ በወንዶች አቤ ጋሻሁን ከአማራ ማረሚያ በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ፣ ታደሰ ወርቁ ከደቡብ ፓሊስ ሁለተኛ እንዲሁም ሚልኬሳ መንገሻ ከሰበታ ክለብ ሶስተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቀዋል።
በሴቶች ደግሞ ፅጌ ገ/ሰላማ ከኢትዮ አትሌትክስ አንደኛ ሆና ስታጠናቅቅ፣ መድን ገ/ስላሴ ከንግድ ባንክ እና ገበያነሽ አያሌው ከመከላከያ ሁለተኛና ሶስተኛ በመሆን ውድድሩን በበላይነት ጨርሰዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ