ከ 50 በላይ ተሳፋሪዎችን የያዘ የመንገደኞች አውሮፕላን ከኢንዶኔዥያ መዲና ጃካርታ ከተነሳ በኋላ ብዙም ሳይቆይ መሰወሩ ተገለጸ ፡፡

306
ከ 50 በላይ ተሳፋሪዎችን የያዘ የመንገደኞች አውሮፕላን ከኢንዶኔዥያ መዲና ጃካርታ ከተነሳ በኋላ ብዙም ሳይቆይ መሰወሩ ተገለጸ ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 01/2013 ዓ.ም (አብመድ) ከምዕራብ ካሊማንታን ክልል ወደ ፖንቲያናክ ሲጓዝ የነበረው የስሪዊጃያ ቦይንግ 737 አውሮፕላን ከበረራ መስመር ጋር ያለው ግንኙነቱ መቋረጡን የሃገሪቱ ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡
የበረራ መከታተያ ድረ ገጽ የሆነው ፍላይት ራዳር 24 ዶት ኮም እንዳመለከተው አውሮፕላኑ ከአንድ ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከ10 ሽህ ጫማ ከፍታ ወይም ከ3ሽህ ሜትር በላይ እየበረረ ባለበት ወቅት ነው የተሰወረው፡፡
የሃገሪቱ ትራንስፖርት ሚኒስቴር በበኩሉ የፍለጋ እና የነፍስ አድን ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጿል፡፡
ስለ አውሮፕላኑ በረራ መረጃ እየተሰበሰበ መሆኑም ተመልክቷል፡፡
የተሰወረው አውሮፕላን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሁለት ትላልቅ አደጋዎች የደረሱበት የቦይንግ ሞዴል አውሮፕላኑ 737 ማክስ አለመሆኑን ቢቢሲ ከደቂቃዎች በፊት ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን የግድቡ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡
Next articleNine senior member of the outlawed Tigray People’s Liberation Front (TPLF) arrested by Ethiopian forces arrived Addis Ababa.