በሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላና ጠራ ወረዳ የሚገነባው የአጅማ-ጫጫ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ፡፡

404
በሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላና ጠራ ወረዳ የሚገነባው የአጅማ-ጫጫ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 01/2013 ዓ.ም (አብመድ) በ5 ቢሊዮን ብር ወጪ በሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላና ጠራ ወረዳ የሚገነባው የአጅማ-ጫጫ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት የመሰረት ድንጋይ በአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር እና በውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጅነር ስለሺ በቀለ (ዶ.ር) ተቀምጧል።
በሦስት ዓመት ውስጥ ግንባታው ይጠናቀቃል የተባለው ፕሮጀክቱ 7ሺህ ሄክታር መሬት ማልማት ያስችላል ነው የተባለው።
ግንባታው በአማራ ውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅትና በቻይና ሲቪል ኢንጅነሪንግ ግንባታ ኮርፖሬሽን (CCEC ) ይከናወናል።
ግድቡ 45ነጥብ 5 ሜትር ከፍታና 372 ሜትር ርዝመት ይኖረዋል።
ዘጋቢ፡- ዘመኑ ታደለ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየኮሮና ቫይረስ የላል ይበላ ከተማ ነዋሪዎችን እንግዳ አስናፍቋቸዋል።
Next articleየፋሲል እና ባሕር ዳር ከነማ እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኞች በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ የመጀመሪያ ምዕራፍ ካሁኑ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚቀርቡ ገለፁ፡፡