“የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እየተሰፋፋ መጥቷል” ጤና ሚኒስቴር

140
“የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እየተሰፋፋ መጥቷል” ጤና ሚኒስቴር
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 30/2013 ዓ.ም (አብመድ) የጤና ሚኒስቴር በኮሮና ቫይረስ መከላከል ዙሪያ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተለያዩ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች እና ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል።
በውይይቱ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ አንዳሉት አሁን ባለው መዘናጋት ምክንያት የኮሮና ቫይረስ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ይገኛል፡፡ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ የኅብረተሰቡ መዘናጋት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ሚኒስቴሩ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ከጥር 3/2013 ዓ.ም ጀምሮ ለቀጣይ ስድስት ወራት ንቅናቄ እንደሚካሂድም አስታውቋል።
በንቅናቄውም የትራንስፖርት መናኸሪያዎች፣ የሃይማኖት ተቋማት የትምህርት ተቋማት እና ሌሎችም ሕዝብ የሚበዛባቸው አካባቢዎች በትኩረት ይቃኛሉ ተብሏል።
በንቅናቄውም የአፍና አፍንጫ ጭምብል በስፋት አገልግሎት ላይ እንዲውል፣ እጅ የመታጠብ እና ሌሎች የጥንቃቄ መንገዶች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ እንደሚካሄድ ተገልጿል።
የምክር ቤት አባላቱም ኅብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የመገናኛ ብዙኃን ኅብረተሰብ የማንቃት እና ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ እንዲያከናውኑና የመንግሥት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ያለ አፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል አገልግሎት እንዳይሰጡ አሳስበዋል፡፡
የመንግሥት ባለስልጣናት ለመከላከሉ ሥራ ግንባር ቀደም ሆነው መሥራት እንደሚገባቸው ተናግረዋል።
በክልል ከተሞች በቫይረሱ ዙሪያ ያለው መዘናጋት እየተባባሰ መምጣቱ ተጠቁሟል።
ዘጋቢ፡- አንዱዓለም መናን – ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበአማራ ክልል ሁሉም አካባቢዎች የልደት በዓል በሰላማዊ ሁኔታ መጠናቀቁን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
Next articleየኮሮና ቫይረስ የላል ይበላ ከተማ ነዋሪዎችን እንግዳ አስናፍቋቸዋል።