በአማራ ክልል ሁሉም አካባቢዎች የልደት በዓል በሰላማዊ ሁኔታ መጠናቀቁን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

94
በአማራ ክልል ሁሉም አካባቢዎች የልደት በዓል በሰላማዊ ሁኔታ መጠናቀቁን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 30/2013 ዓ.ም (አብመድ) የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ትናንት ተከብሮ ውሏል፡፡ በዓሉ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች በሰላም መጠናቀቁን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የኮምዩኒኬሽን እና ሚዲያ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር መሰረት ደባልቄ ለአብመድ ተናግረዋል፡፡
የፀጥታ ኃይሉ የልደት በዓል በሰላማዊ መንገድ እንዲከበር ለማድረግ በቂ ቅድመ ዝግጅት አድርጎ ነበር ያሉት ኮማንደር መሰረት በዓሉም በእቅዱ መሰረት ሰላማዊ ሆኖ ተጠናቋል ብለዋል፡፡ በቀጣይም የሚከበረው የጥምቀት በዓል በተመሳሳይ መልኩ እንዲከበር ቀድሞ ዝግጅት መደረጉንም ጠቁመዋል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሕዝባዊ በዓላት ላይ የወጣቶች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የማኅበረሰቡ እና የፀጥታ ኃይሉ ቅንጅት ትርጉም ያለው ለውጥ መፍጠሩ እየተስተዋለ ነው ተብሏል፡፡
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በፀጥታ ሥራው ተሰማርተው አመርቂ ውጤት ላመጡ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች፣ ለሃይማኖት አባቶች፣ ለሀገር ሽማግሌዎች እና ለክልሉ የፀጥታ ኃይል አባላት ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
በልደት በዓል በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች የእሳት አደጋም ሆነ ወንጀል ነክ ድርጊቶች አልተከሰቱም ተብሏል፡፡ ከትራፊክ አደጋ ጋር ተያይዞ ግን በላልይበላ ሁለት ሰዎች የመንሸራተት እና መውደቅ አደጋ ገጥሟቸው ህይዎታቸው ሲያልፍ፤ አንድ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ወደኋላ ተንሸራትቶ ደግሞ 12 ሰዎች ላይ ቀላል አደጋ መድረሱን ኮማንደር መሰረት ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየኮሮናቫይረስን በመከላከል ላይ ያተኮረ ንቅናቄ ከጥር 3 ጀምሮ ለስድስት ወራት እንደሚካሄድ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
Next article“የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እየተሰፋፋ መጥቷል” ጤና ሚኒስቴር