የኮሮናቫይረስን በመከላከል ላይ ያተኮረ ንቅናቄ ከጥር 3 ጀምሮ ለስድስት ወራት እንደሚካሄድ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

129
የኮሮናቫይረስን በመከላከል ላይ ያተኮረ ንቅናቄ ከጥር 3 ጀምሮ ለስድስት ወራት እንደሚካሄድ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 30/2013 ዓ.ም (አብመድ) ለስድስት ወራት በሚቆየው በዚህ ንቅናቄ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግን ጨምሮ የኮሮናቫይረስ መከላከያ ዘዴዎችን በአግባቡ በመተግበር ላይ ትኩረት ይደረጋል ተብሏል።
በነዚህ ወራት “እንድናገለግልዎ ማስክዎን ያድርጉ (No Mask, No Service)” የሚል ንቅናቄ እንደሚካሄድ እና በንቅናቄው ወቅትና ከዚያም በኋላ የሚያገለግሉ ጭምብሎችን የማሰባሰብ ሥራ እንደሚከናወን ተገልጿል።
ንቅናቄው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ትምህርት ቤቶች፣ በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ በትራንስፖርት መናኸሪያ ስፍራዎች፣ በገበያ ቦታዎች፣ በሃይማኖት ተቋማትና ሕዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው መሰል ስፍራዎች ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ተጠቁሟል።
በንቅናቄው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም በቁጥጥርና ክትትል ሥራ እንዲሁም በግንዛቤ ማስጨበጥ ተግባር ላይ በኃላፊነት እንደሚንቀሳቀሱ መገለፁን ኢብኮ ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየፕሬዝዳንት ትራምፕ ደጋፊዎች የመንግሥት መቀመጫና የሁለቱ ምክር ቤቶች አዳራሾች የሚገኙበትን ካፒቶል ሒልን ጥሰው መግባታቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያውያን ድርጊቱን በማውገዝ ላስተላለፉት መልዕክት ምስጋና ቀረበ፡፡
Next articleበአማራ ክልል ሁሉም አካባቢዎች የልደት በዓል በሰላማዊ ሁኔታ መጠናቀቁን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡