ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ከጦር አካል ጉዳተኞች ጋር የልደት በዓልን እያከበሩ ነው፡፡

172
ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ከጦር አካል ጉዳተኞች ጋር የልደት በዓልን እያከበሩ ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 29/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሚኒስትሮችና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ከጦር አካል ጉዳተኞች ጋር የልደት በዓልን እያከበሩ ነው።
በሀገር መከላከያ ሰራዊት እንዲሁም በሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርና በአዲስ አበባ ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ በትብብር ባዘጋጁት በጋራ በዓል የማክበር ሥነ-ሥርዓት ላይ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ታድመዋል።
ልደታ በሚገኘው የአካል ጉዳተኞች ተሀድሶ ማዕከል በሚከበረው በዓል ላይ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ እና የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ተገኝተዋል። የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች ተገኝተዋል። ኢዜአ እንደዘገበው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article‹‹ድርጊቱ የታላቋን አሜሪካ ክብር የማይመጥን አሳፋሪ ተግባር ነው›› የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን
Next article“በእምዬ ምኒልክ በከበረው ንጉሥ፣ በኃይለስላሴ በከበረው ንጉሥ፣ ጤፉን በልተህ እንደሁ መቋጠሪያ መልስ”