በበጎ ፈቃድ የማኅበረሰብ አገልግሎት የሚሰማሩ ወጣቶች ለስልጠና ወደ ዩኒቨርሲቲዎች እየገቡ መሆኑን የሠላም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

318

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 28/2013 ዓ.ም (አብመድ) ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ወጣቶች ሀገራዊ ተልዕኮዎችን ለማሳካት የማይተካ ሚና አላቸው ብሏል።

የወጣቶችን አቅም በመገንባት፣ ክህሎታቸውን ማዳበር እና እምቅ አቅማቸውን ለሀገር ግንባታ ማዋል ለነገ የማይተው ተግባር መሆኑን መንግሥት በፅናት እንደሚያምን ገልጿል፡፡ በዚህም የሠላም ሚኒስቴር ብሔራዊ የወጣቶች በጎ ፈቃድ የማኅበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም መንደፉን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ጠቅሷል፡፡

በ22 ዩኒቨርሲቲዎች ለ45 ቀናት ስልጠና በመስጠት ወጣቶቹ በበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ላይ ተሰማርተው ሀገራቸውንና ወገናቸውን እንዲያገለግሉ ተመቻችቷል ተብሏል። በዚህም ወጣቶቹ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ወደ ተመደቡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ለስልጠና እየገቡ እንደሆነም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል።

እንደ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ መረጃ የበጎ ፈቃድ የማኅበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ወጣቶቹ መልካም ስብዕና፣ አመለካከትና የሥራ ባህል ግንባታን ይፈጥራል፡፡ በቀጣዮቹ 10 ወራት ከሚያውቋቸው አካባቢዎች ርቀው በሚመደቡባቸው የተለያዩ አካባቢዎችና ማኅበረሰቦች መካከል የበጎ ፈቃድ ተግባራትን በማከናወን ኢትዮጵያዊ የሆኑ መልካም እሴቶችን በማጋራት እና በመጋራት ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር ያለመ ፕሮግራም ነው ተብሏል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleበባሕር ዳር ከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች የምግብ ድጋፍ ተደረገ።
Next article“በዓሉን ስናከብር የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆችን በማሰብን በመርዳት ሊሆን ይገባል” የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር