
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 28/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
የዘንድሮውን በዓል የምናከብረው የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት የምንጊዜም ጠላት የሆነውን የትህነግ ወራሪ፣ ተስፋፊና አሸባሪ ቡድን በተደመሰሰበትና ሕግና ስርዓት እየተከበረ ባለበት ወቅት ነው ብለዋል ርእሰ መሥተዳድሩ።
የአማራ ሕዝብ የጥቃት ዒላማ መሆኑ ቀጥሎ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍል የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች እየተሳደዱና በግፍ እየተፈናቀሉ ያሉበት ወቅት መሆኑንም ርእሰ መሥተዳድሩ ተናግረዋል።
የልደት በዓልን ስናከብርም አንድነታችንን የሚሸረሽሩ ኃይሎችን በመታገል፣ የተፈናቀሉ ወገኖችን በመጠየቅና በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባም ጥሪ አቅርበዋል።
የክልሉ መንግሥት የአማራ ሕዝብን ጥቅምና ክብር ለማስጠበቅ ከምንጊዜውም በበለጠ ቁርጠኝነት እየሠራ ነው፤ሕዝቡም ተባባሪ መሆን አለበት ብለዋል ርእሰ መስተዳድሩ።
የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የሰላምና የደስታ እንዲሆንም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡- ስማቸው እሸቴ – ከፍኖተ ሰላም
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ