የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ተመሥገን ጥሩነህ የልደት በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

275
ዳይሬክተሩ በይፋዊ ትስስር ገጻቸው ያስተላለፉት ሙሉ መልዕክት
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ። የክርስቶስ ልደት እውነተኛ ዜናና የሐሰት ዜና የተፎካከሩበት ዜና ነው። መላዕክት እና የጥበብ ሰዎች ዓለምን የሚያድነው ንጉሥ ተወልዷል አሉ። ሄሮድስና አይሁድ ዓለምን የሚያድነው ንጉሥ ከቤተልሔም ሕጻናት ጋር አብሮ ተገድሏል አሉ።
ሐሰት መሸነፏ ላይቀር ለጊዜው እንደ ፈንድሻ ደምቃ ትታያለች ፤ ለጊዜው ታስደስታለች። በዚህም የተነሣ ብዙዎች ይቀባበሏታል። ፈንድሻ ግን ምግብም፣ ጤናም፣ ኃይልም አትሆንም። አንዳንዶች ውሸት የዕለት እንጀራቸው ሆኗል። በውሸት በምትገኘው የፈንድሻ ደስታ ሰክረዋል። ለሌሊት ብርሃናማዋ ፀሐይ ፣ ለውሸት ደስታም እውነት እስክትገለጥ ብቻ ነው።
የሐሰት ብር ምንም ያህል ተመሳስሎ ቢሠራ እውነተኛ ብር አይሆንም። ለጊዜው ያሳስታል እንጂ እንዳሳሳተ አይዘልቅም። ሐሰትን የጦር መሣሪያቸው አድርገው ሀገርንና ዓለምን በሚያሸብሩት ላይ የእውነት ባውዛ እናብራባቸው። የጨለማ ለምዳቸውን በእውነት ፀሐይ ገፍፈን ሐሰት ዕርቃኗን እንድትቆም እናድርግ።
እውነቱ እየተገለጠ ሲሄድ አንገታቸውን የሚደፉ እንዳይበዙ ፤ ሁሌም ቢመርም ለእውነት መቆም ክብር ነው።
ሀገርንና ትውልድን በእውነት እንታደግ።
መልካም በዓል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“ኅብረተሰቡ በግብይት ወቅት በሀሰተኛ የብር ኖት እንዳይታለል ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅበታል” አቶ ዓለሙ እንዳለው የዓባይ ባንክ ሽምብጥ ቅርንጫፍ ጊዜያዊ ሥራ አስኪያጅ
Next articleየአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህመት ለልደት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡